1 ሳሙኤል 30:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ከመሆኑ በፊት በይሁዳ ደቡብ የምትገኘውን የከሪታውያንን ግዛትና የካሌብን ግዛት በመውረር ጺቅላግን አቃጥለናታል” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከሊታውያንን ደቡብ፣ የይሁዳን ግዛትና የካሌብን ደቡብ ወረርን፤ ጺቅላግንም በእሳት አጋየናት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከሪታውያንን ደቡብ፥ የይሁዳን ግዛትና የካሌብን ደቡብ ወረርን፤ ጺቅላግንም በእሳት አጋየናት።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛም በከሊታውያን አዜብ፥ በይሁዳም በኩል፥ በካሌብም አዜብ ላይ ዘመትን፥ ሴቄላቅንም በእሳት አቃጠልናት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛም በከሊታውያን ደቡብ፥ በይሁዳም ምድር፥ በካሌብም ደቡብ ላይ ዘመትን፥ ጺቅላግንም በእሳት አቃጠልናት አለ። |
ስለዚህ ካህኑ ሳዶቅ፥ ነቢዩ ናታን፥ የዮዳሄ ልጅ በናያና የንጉሡ ክብር ዘበኞች ሰሎሞንን ዳዊት በሚቀመጥባት በቅሎ ላይ በማስቀመጥ ወደ ግዮን ምንጭ ወረዱ፤
ንጉሡም እርሱን ያጅቡት ዘንድ ካህኑን ሳዶቅን፥ ነቢዩን ናታንን፥ የዮዳሄን ልጅ በናያንና የቤተ መንግሥቱን ክብር ዘበኞች ልኮአል፤ እነርሱም ንጉሡ በሚቀመጥባት በቅሎ ላይ እንዲቀመጥ አድርገውታል።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በፍልስጥኤማውያን ላይ ኀይሌን እጠቀማለሁ፤ ብሪታውያንን እፈጃለሁ፤ በባሕር ጠረፍ የቀሩትንም አጠፋለሁ።
እናንተ በባሕር ዳር የምትኖሩ ከሪታውያን ማለት ፍልስጥኤማውያን ወዮላችሁ! የእግዚአብሔር ፍርድ በእናንተ ላይ ደርሷል፤ የፍልስጥኤም ምድር ለሆንሽው ከነዓን ወዮልሽ አንድ እንኳ ነዋሪ እንዳይኖርብሽ አድርጌ አጠፋሻለሁ።
እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት ለይፉኔ ልጅ ለካሌብ ከይሁዳ ነገድ ኪርያት ዐርባን ወይም ኬብሮን እርስት አድርጎ ሰጠው። (አርባ የዐናቅ አባት ነበር)
ዳዊትና ተከታዮቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ ሲደርሱ ዐማሌቃውያን ኔጌብንና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ በጺቅላግም ላይ አደጋ ጥለው አቃጠሉአት።
ዳዊትም ወጣቱን “የማን አገልጋይ ነህ? አመጣጥህስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቀው። ወጣቱም “እኔ ግብጻዊ የሆንኩ የአንድ ዐማሌቃዊ አገልጋይ ነኝ፤ ታምሜ ስለ ነበር ከሦስት ቀን በፊት ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ፤
ዳዊትም “እነዚያ ወራሪዎች ወዳሉበት ስፍራ ልትመራን ትችላለህን?” ሲል ጠየቀው። ወጣቱም “እንደማትገድለኝና ለጌታዬም አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ ከማልክልኝ ላሳይህ እችላለሁ” ሲል መለሰለት።
ከዚያም በኋላ ዳዊትን ወራሪዎቹ ወዳሉበት እየመራ አደረሰው። ወራሪዎቹም በየቦታው ተበታትነው በመብላትና በመጠጣት ተድላ ደስታ በማድረግ ላይ ነበሩ፤ ከፍልስጥኤምና ከይሁዳ ያገኙት ምርኮ እጅግ ብዙ ነበር፤