እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው፦ “በንጹሕ ኅሊና እንዳደረግህ ዐውቄአለሁ፤ ወደ እርስዋ ቀርበህ በእኔ ፊት ኃጢአት እንዳትሠራ ያደረግኩህም ስለዚህ ነው።
1 ሳሙኤል 25:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበቀል እርምጃ በመውሰድ ጠላቶችህን እንዳትገድል የጠበቀህ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ እኔ አሁን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ ጠላቶችህና አንተን ለመጒዳት የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ቅጣታቸውን ይቀበሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታዬ ሆይ፤ ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ደም ከማፍሰስና በገዛ እጅህ ከመበቀል የጠበቀህ እግዚአብሔር ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና ጌታዬን ሊጐዱ የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታዬ ሆይ፤ በሕያው ጌታ፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ደም ከማፍሰስና በገዛ እጅህ ከመበቀል የጠበቀህ ጌታ ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና ጌታዬን ሊጐዱ የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ጌታዬ ሆይ! ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ወደ ንጹሕ ደም እንዳትገባና፥ እጅህን እንድታድን የከለከለህ እግዚአብሔር ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፥ ጌታዬ ሆይ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ! ወደ ደም እንዳትገባ፥ እጅህም ራስህን እንዳታድን የከለከለህ እግዚአብሔር ነው፥ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ። |
እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው፦ “በንጹሕ ኅሊና እንዳደረግህ ዐውቄአለሁ፤ ወደ እርስዋ ቀርበህ በእኔ ፊት ኃጢአት እንዳትሠራ ያደረግኩህም ስለዚህ ነው።
ንጉሡም “ወጣቱ አቤሴሎም ምንም ጒዳት አልደረሰበትምን?” ሲል ጠየቀ። አገልጋዩም “ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ላይ የደረሰ ነገር በጠላቶችህና በአንተ ላይ በዐመፁት ሁሉ ላይ ይድረስ!” ሲል መለሰ።
በመንገድም ሳሉ ኤልያስ ኤልሳዕን “እነሆ፥ አንተ በዚህ ቈይ፤ እኔ ወደ ቤትኤል እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ከቶ ከአንተ አልለይም” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ቤትኤል ሄዱ።
ማድጋዎቹንም ሁሉ ከሞሉ በኋላ “ሌላ ትርፍ የለም ወይ?” ስትል ጠየቀች፤ ከልጆችዋም አንዱ “ሌላ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም በኋላ ዘይቱ መውረዱን አቆመ፤
እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።
ከኢየሩሳሌም ተማርከው ወደ ባቢሎን የተሰደዱ ሕዝብ ሁሉ በአንድ ሰው ላይ የእርግማን ቃል መናገር ሲፈልጉ፥ ‘እግዚአብሔር የባቢሎን ንጉሥ በሕይወት እንደ ጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ ያድርግህ’ ይላሉ፤
በዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል እጅግ ከመደንገጡና በሐሳብ ከመታወኩ የተነሣ ለጥቂት ጊዜ ዝም አለ፤ ንጉሡም “ብልጣሶር ሆይ! ሕልሙም ሆነ ትርጒሙ አያስጨንቅህ” አለው። ብልጣሶርም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! ሕልሙም ሆነ ትርጒሙ ለአንተ መሆኑ ቀርቶ ለጠላቶችህ ቢሆን በወደድሁ ነበር።
“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ተገቢ ዋጋን እከፍላለሁ” ያለው ማን መሆኑን እናውቃለን፤ እንዲሁም “እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል ጌታ።
ሐናም ዔሊን እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ ሆይ፥ ዕድሜህን ያርዝመውና አንድ ጊዜ እዚህ በፊትህ ቆሜ ወደ እግዚአብሔር ስጸልይ ያየኸኝ ሴት እኔ ነኝ፤
ዳዊት ግን “አባትህ አንተ እኔን ምን ያኽል እንደምትወደኝ በደንብ ያውቃል፤ ስለዚህም ዕቅዱን አንተ እንድታውቅበት ላለማድረግ ወስኖአል፤ ይህንንም የሚያደርገው አንተ ይህን ብታውቅ በብርቱ እንደምታዝን ስለሚያውቅ ነው፤ በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከአሁን ወዲያ ወደ ሞት ለመድረስ የቀረችን አንዲት ዕርምጃ ብቻ ናት!” አለው።
ዳዊትም ከዚያ ተነሥቶ በሞአብ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ የሞአብንም ንጉሥ “እግዚአብሔር ለእኔ የሚያደርግልኝን ነገር እስካውቅ ድረስ እባክህ አባቴና እናቴ መጥተው በአንተ ዘንድ እንዲቈዩ ፍቀድላቸው” ሲል ጠየቀው።
የናባልን ጉዳይ ከቁም ነገር አታግባው! እርሱ ልክ እንድ አስሙ አጠራር ሞኝ ነው! ጌታዬ፥ የአንተ አገልጋዮች በመጡ ጊዜ እኔ በዚያ አልነበርኩም፤
ዳዊትም የናባልን መሞት በሰማ ጊዜ “እኔን በመስደቡ እግዚአብሔር ናባልን ስለ ተበቀለውና እኔንም ከስሕተት ስለ ጠበቀኝ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱ ናባልን ስለ ክፉ ሥራው ቀጥቶታል” አለ። ከዚህም በኋላ ዳዊት ወደ አቢጌል መልእክተኛ ልኮ ሊያገባት መፈለጉን ገለጠላት።
በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ራሱ ሳኦልን ይገድለዋል፤ የሚሞትበት ጊዜ ደርሶ፥ አለበለዚያም በጦርነት መሞቱ አይቀርም፤