ባልዋ ግን “ዛሬ ስለምን ትሄጂአለሽ? ሰንበት ወይም የጨረቃ በዓል የሚከበርበት ጊዜ አይደለም” አላት። እርስዋም “ግድ የለም፤ እንዳልኩህ አድርግ” አለችው፤
1 ሳሙኤል 20:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት በዓል ነው፤ እኔም ከንጉሡ ጋር መብላት ይኖርብኛል፤ እስከ ነገ ወዲያ ምሽት ድረስ እንድደበቅ ፍቀድልኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊት እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ነገ የወር መባቻ በዓል ስለ ሆነ፣ ከንጉሡ ጋራ ምሳ መብላት ይጠበቅብኛል፤ ነገር ግን እስከ ከነገ ወዲያ ማታ ድረስ ከዱር ልደበቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዳዊት እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ነገ የወር መባቻ በዓል ስለሆነ፥ ከንጉሡ ጋር ምሳ መብላት ይጠበቅብኛል፤ ነገር ግን እስከ ከነገ ወዲያ ማታ ድረስ ከዱር ልደበቅ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ዮናታንን አለው፥ “እነሆ ነገ መባቻ ነው፤ በንጉሥም አጠገብ ለምሳ አልቀመጥም፤ እስከ ማታ ድረስ በውጭ በሜዳ እንድሸሸግ አሰናብተኝ ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ዮናታንን አለው፦ እነሆ፥ ነገ መባቻ ነው፥ በንጉሥም አጠገብ ለምሳ አልቀመጥም፥ እስከ ሦስተኛው ቀን ማታ ድረስ በውጭ በሜዳ እንድሸሸግ አሰናብተኝ። |
ባልዋ ግን “ዛሬ ስለምን ትሄጂአለሽ? ሰንበት ወይም የጨረቃ በዓል የሚከበርበት ጊዜ አይደለም” አላት። እርስዋም “ግድ የለም፤ እንዳልኩህ አድርግ” አለችው፤
የሚሰድበኝ ጠላት አይደለም፤ ጠላት ቢሆንማ ኖሮ በታገሥኩ ነበር። የሚታበይብኝም ባለጋራ አይደለም፤ ባለጋራ ቢሆንማ ኖሮ ከፊቱ በተሰወርኩ ነበር።
እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህላችንን መሸጥ እንድንችል የወር መባቻው በዓል ምነው ቶሎ ባለፈልን! ስንዴ ወደ ገበያ ለመውሰድ ሰንበትም መቼ ያልፍልናል? በዓላቱ ካለፉልን የእህሉን መስፈሪያ አሳንሰን ከፍተኛ ዋጋ እንጠይቃለን፤ በሐሰተኛ ሚዛንም ሕዝቡን እናታልላለን፤
እንዲሁም በደስታ በዓሎቻችሁ፥ ማለት በወር መጀመሪያና በሌሎችም የተወሰኑ በዓሎቻችሁ፥ በሚቃጠል መሥዋዕትና በአንድነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶችን ትነፋላችሁ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ስለ እናንተ አስታዋሾች ይሆናሉ። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
“በእያንዳንዱ ወር መጀመሪያ ቀን የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ይኸውም ነውር የሌለባቸውን ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ።
በእርሱ ላይ የታቀደውን ነገር ሁሉ እንዲህ ሲል ነገረው፥ “አባቴ ሊገድልህ ዐቅዶአል፤ ስለዚህ እባክህ በነገው ማለዳ ይህ እንዳይደርስብህ ተጠንቀቅ፤ ስውር በሆነ ቦታ ተሸሽገህ ቈይ፤
አዲስ ጨረቃ የታየችበት በዓል ካለፈ በኋላም በተከታዩ ቀን የዳዊት ወንበር ባዶ ነበር፤ ስለዚህ ሳኦል ልጁን ዮናታንን “የእሴይ ልጅ ትናንትም፥ ዛሬም ወደዚህ ግብዣ ያልመጣው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።
“ምናልባት አባትህ ቢፈልገኝ በቤተሰቡ ዓመታዊ በዓል የሚከበር ስለ ሆነ ወደ ቤተልሔም እንዲሄድ እፈቅድለት ዘንድ ዳዊት እኔን አጥብቆ ለምኖኛል ብለህ ንገረው።