1 ሳሙኤል 14:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም ወታደሮቹን “እንግዲህ እንውረድና በፍልስጥኤማውያን ላይ በሌሊት አደጋ እንጣልባቸው፤ እስኪነጋም ድረስ ሀብታቸውን ዘርፈን ሁሉንም እንፍጃቸው” አለ። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” አሉት። ካህኑ ግን “በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንጠይቅ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ “ፍልስጥኤማውያንን ተከትለን በሌሊት እንውረድና እስኪነጋ ድረስ እንበዝብዛቸው፤ አንድም ሰው በሕይወት አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም፣ “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፣ “እዚሁ እግዚአብሔርን እንጠይቅ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ ሳኦልም፥ “ፍልስጥኤማውያንን ተከትለን በሌሊት እንውረድና እስኪ ነጋ ድረስ እንዝረፋቸው፤ አንድም ሰው በሕይወት አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፥ “ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፥ “ፍልስጥኤማውያንን በሌሊት ተከትለን እንውረድ፤ እስኪነጋም ድረስ እንበዝብዛቸው፤ አንድ ሰው እንኳ አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም፥ “ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አድርግ” አሉት። ካህኑም፥ “ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፥ ፍልስጥኤማውያንን በሌሊት ተከትለን እስኪነጋ ድረስ እንበዝብዛቸው አንድ ሰው እንኳ አናስቀርላቸው አለ። እነርሱም፦ ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አድርግ አሉት። ካህኑም፦ ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ አለ። |
ሆኖም ዕለት በዕለት ይሹኛል፤ መንገዶቼንም ማወቅ ደስ ይላቸዋል፤ ጽድቅን እንደሚያዘወትሩና የእኔን የአምላካቸውን ትእዛዝ እንዳልተወ ሕዝብ ከእኔ ትክክለኛውን ፍርድ ይለምናሉ፤ ወደ እኔ ወደ አምላክም በመቅረብ ይደሰታሉ።”
ካህኑ አልዓዛር በኡሪም አማካይነት ፈቃዴን የሚያውቅ ስለ ሆነ ኢያሱ በአልዓዛር ይደገፋል፤ በዚህም ዐይነት አልዓዛር ኢያሱንና መላውን የእስራኤል ማኅበር በተግባር አፈጻጸማቸው ሁሉ ይመራቸዋል።”
እናንተ ግን በዚያ አትቈዩ፤ ጠላትን እያሳደዳችሁ ከኋላ በኩል አደጋ መጣላችሁን ቀጥሉ፤ ሸሽተው ወደ ከተሞቻቸው እንዲገቡ መንገድ አትስጡአቸው! አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ድልን ያቀዳጃችኋልና።”
የእስራኤል ሕዝብ ዋጋ ያለውን ንብረትና ከብቱን ሁሉ ከእነዚህ ከተሞች ወስደው የራሳቸው ንብረት አደረጉት፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ፤ አንድ ሰው እንኳ ሳይቀር ሁሉንም ገደሉ።
ሕልቃናም “ጥሩ ነው፤ መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ፤ ጡት እስክታስጥይውም ድረስ በቤት መቈየት ትችያለሽ፤ እግዚአብሔር የሰጠሽን የተስፋ ቃል ይፈጽምልሽ” ሲል መለሰላት፤ ስለዚህም ሐና በቤት ተቀምጣ ልጇን ታሳድግ ጀመር።
በማግስቱ ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ከፈለ፤ ከማለዳ ጀምሮ ባለው ጊዜ በአሞናውያን ሰፈር ላይ አደጋ ጥለው ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ ፈጁአቸው፤ ከእልቂት የተረፉትም ተበታትነው ለየብቻቸው ሸሹ።
በሴሎ የእግዚአብሔር ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ ካህኑ ፊንሐስ የወለደው የኢካቦድ ወንድም የአሒጡብ ልጅ አኪያ ኤፉድ ለብሶ ከእርሱ ጋር አብሮ ነበር። እነርሱም ዮናታን ወዴት እንደ ሄደ አላወቁም ነበር።