ለእግዚአብሔርም መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ አቀረበ፤ እግዚአብሔርም የዳዊትን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የወረደውም የቸነፈር መቅሠፍት ከዚህ በኋላ ቆመ።
1 ሳሙኤል 13:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ሳኦል ሕዝቡን “የሚቃጠለውንና ለደኅንነት የሚሆነውን የአንድነት መሥዋዕት አምጡልኝ” ብሎ በማዘዝ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ሳኦል፣ “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕቱን አምጡልኝ” አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ሳኦል፥ “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕቱን አምጡልኝ” አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፥ “የሚቃጠል መሥዋዕትና የደኅንነት መሥዋዕት አምጡልኝ” አለ። የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አሳረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ የሚቃጠል መሥዋዕትና የደኅንነት መሥዋዕት አምጡልኝ አለ። |
ለእግዚአብሔርም መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ አቀረበ፤ እግዚአብሔርም የዳዊትን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የወረደውም የቸነፈር መቅሠፍት ከዚህ በኋላ ቆመ።
ታላቅ መሠዊያ የሚገኘው በገባዖን ስለ ነበር አንድ ቀን ሰሎሞን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ፤ ከዚህም በፊት በዚያ መሠዊያ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦአል፤
ዐመፀኞች የሚያቀርቡት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው፤ በተለይም በክፉ አሳብ ተነሣሥተው የሚያቀርቡለት መሥዋዕት የበለጠ አጸያፊ ነው።
“ለእኔ በሬ ሲሠዉ በሌላ በኩል የሰውን ሕይወት ያጠፋሉ፤ ለእኔ ጠቦት ሲሠዉ ለጣዖትም ውሻ ያቀርባሉ፤ ለእኔ የእህል መሥዋዕት ሲያቀርቡ፤ የዕሪያ ደምም ለጣዖት ያቀርባሉ፤ ለእኔ ዕጣን ያጥናሉ፤ ጣዖቶቻቸውንም ያመሰግናሉ፤ የራሳቸውን አካሄድ በመምረጥ በርኲሰታቸው ይደሰታሉ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤
እዚያም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትንና የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን፥ የከብቶቻችሁንና የበጎቻችሁን በኲር ታቀርባላችሁ፤