1 ጴጥሮስ 1:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም የማይጠፋውን፥ የማይበላሸውንና የማያረጀውን ርስት በሰማይ አዘጋጅቶላችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በሰማይ ለማይጠፋ፣ ለማይበላሽና ለማይለወጥ ርስት እንደ ገና ወለደን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም የማያልፍም፥ እድፈትም የሌለበት፥ የማይጠፋ ርስት በሰማይ ቀርቶላችኋል። |
በፈሳሹ ውሃ ዳርና ዳር ለምግብ የሚሆኑ ተክሎች በየዐይነቱ ይገኛሉ፤ እነርሱም ቅጠሎቻቸው አይደርቁም፤ ፍሬ ማፍራትንም አያቋርጡም፤ ከቤተ መቅደሱ ሥር የሚፈሰውን ወንዝ ውሃ ስለሚያገኙ በየወሩ አዲስ ፍሬ ያፈራሉ፤ ዛፎቹ ፍሬአቸው ለምግብ፥ ቅጠላቸው ለፈውስ የሚጠቅም ነው።”
በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!
ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ በመሄድ ላይ ሳለ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ በፊቱ ተንበረከከና “ቸር መምህር ሆይ፥ የዘለዓለምን ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባኛል?” ሲል ጠየቀው።
ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’
እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን የእርሱ ወራሾች ነን፤ ከክርስቶስም ጋር እንወርሳለን፤ አሁን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች ብንሆን በኋላ የክብሩ ተካፋዮች እንሆናለን።
በሩጫ የሚወዳደሩ ሁሉ አድካሚ ልምምድ ያደርጋሉ፤ እነርሱ እንዲህ የሚደክሙት የሚጠፋውንና ጊዜያዊ የሆነውን አክሊል ለማግኘት ነው፤ እኛ ግን የምንደክመው የማይጠፋውንና ዘለዓለማዊ የሆነውን አክሊል ለማግኘት ነው።
አንድ ነገር የሚወረሰው በሕግ አማካይነት ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል አማካይነት መሆኑ በቀረ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ውርስን ለአብርሃም የሰጠው በተስፋው ቃል አማካይነት ነው።
ለምን ዐይነት ተስፋ እንደ ተጠራችሁና ቅዱሳን የሚወርሱት ክቡር ርስት ምን ያኽል ብዙ እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ የልቡናችሁ ዐይን እንዲበራላችሁ እጸልያለሁ።
የእውነት ቃል የሆነው ወንጌል በመጀመሪያ ወደ እናንተ በደረሰ ጊዜ በእርሱ ያለውን ተስፋ ሰምታችኋል፤ ስለዚህ እምነታችሁና ፍቅራችሁ የተመሠረተው በሰማይ ተዘጋጅቶ በሚቈያችሁ በዚህ ተስፋ ላይ ነው።
ከእንግዲህ ወዲህ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ይህንንም አክሊል ያ ትክክለኛ ፍርድን ፈራጁ ጌታ በዚያን ቀን ይሰጠኛል፤ የሚሰጠውም ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእርሱን መገለጥ ለሚወድዱ ሁሉ ነው።
እናንተ የተሻለና ነዋሪ ሀብት በሰማይ እንዳላችሁ በማወቃችሁ ለእስረኞች ራራችሁላቸው፤ ንብረታችሁም ሲወሰድባችሁ ታግሣችሁ ሁኔታውን በደስታ ተቀበላችሁ።
እነዚያ የተጠሩት እግዚአብሔር በተስፋ የሰጠውን ዘለዓለማዊ ርስት እንዲቀበሉ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን ማእከላዊ አስማሚ ሆኖአል፤ ይህም የሆነው ሰዎችን በመጀመሪያው ቃል ኪዳን ሥር ሆነው ከሠሩት ኃጢአት ለማዳን እርሱ በመሞቱ ነው።
ጸያፍ የሆነ ነገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ርኲሰትን የሚያደርግና ውሸት የሚናገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ወደ እርስዋ የሚገቡ ስሞቻቸው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፉ ብቻ ናቸው።