Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 31:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በአንተ ለመከለል ወደ አንተ ለሚጠጉ በሰዎች ሁሉ ፊት የምትሰጠው ለሚፈሩህ ያዘጋጀኸው ደግነት ምንኛ ትልቅ ነው!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በሰዎች ልጆች ፊት፣ ለሚፈሩህ ያስቀመጥሃት፣ መጠጊያ ላደረጉህም ያዘጋጀሃት፣ በጎነትህ ምንኛ በዛች!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በድፍረትና በትዕቢት በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 31:19
24 Referencias Cruzadas  

ይሁን እንጂ መጽሐፍ፥ “የሰው ዐይን ያላየውን፥ የሰው ጆሮ ያልሰማውን፥ የሰው ልብ ያላሰበውን፥ እግዚአብሔር ለሚወዱት አዘጋጅቶአል” ይላል።


ከጥንት ጀምሮ ተስፋቸውን በእርሱ አድርገው ለሚተማመኑበት ወገኖች እነዚያን ሁሉ ድንቅ ነገሮች ያደረገ አምላክ ከአንተ በቀር አልተሰማም፤ አልታየም፤ የተረዳም የለም።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ፊት ሙሉ ደስታ፥ በቀኝህም የዘለዓለም እርካታ ይገኛል።


በጠላቶቼ ፊት ታላቅ ማእድ አዘጋጀህልኝ፤ ራሴን በዘይት ትቀባልኛለህ፤ ጽዋዬም እስኪትረፈረፍ ድረስ ይሞላል።


ለዚህም ነገር ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው፤ ከዚያም በላይ ለሚሰጠን ነገር ሁሉ ዋስትና እንዲሆን መንፈሱን የሰጠንም እርሱ ነው።


እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።


እውነት የሆነውን ነገር የሚያደርግ ግን ወደ ብርሃን ይመጣል፤ ወደ ብርሃን የሚመጣውም ያደረገው ነገር በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት መሆኑ በግልጥ እንዲታይ ነው።”


ልባቸው ንጹሕ ለሆነ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ቸር ነው።


አምላክ ሆይ፥ ሰላምን አሰፈንክልን፤ ሥራችንን ሁሉ የፈጸምክልን አንተ ነህ።


አምላክ ሆይ! ኀይልህን ግለጥ፤ ከዚህ በፊት እኛን ያዳንክበትን ብርታትህን አሳይ።


እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና አስፈሪነት ተመልከቱ፤ አስፈሪነቱን የሚያሳየው በወደቁት ላይ ሲሆን ቸርነቱን የሚያሳየው ግን ለእናንተ ነው፤ ይህንንም የሚያደርገው እርሱን በማመን ጸንታችሁ ብትኖሩ ነው፤ ባትጸኑ ግን እናንተም ተቈርጣችሁ ትወድቃላችሁ።


እናንተ የተሻለና ነዋሪ ሀብት በሰማይ እንዳላችሁ በማወቃችሁ ለእስረኞች ራራችሁላቸው፤ ንብረታችሁም ሲወሰድባችሁ ታግሣችሁ ሁኔታውን በደስታ ተቀበላችሁ።


በዚህ ጊዜ ጉባኤው ጸጥ ብሎ በርናባስና ጳውሎስ በእነርሱ አማካይነት እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ተአምርና ድንቅ ነገር ሁሉ ሲናገሩ በመገረም አዳመጣቸው።


በያዕቆብ ልጆች ላይ ምንም ዐይነት ጥንቈላ፥ በእስራኤልም ላይ ምንም ዐይነት አስማት አይሠራም፤ እነሆ፥ አሁን ለያዕቆብና ለእስራኤል፥ ‘እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ ተመልከቱ!’ ይባላል።


እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios