1 ዮሐንስ 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞች ሆይ! ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ፥ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞች ሆይ፥ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞች ሆይ፥ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ። |
በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።
ይህን ለእናንተ መናገሬ በእኔ ሆናችሁ ሰላም እንዲኖራችሁ ብዬ ነው፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፥ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”
ጴጥሮስም ሰዎቹን ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ! በዚህ ነገር ስለምን ትደነቃላችሁ? ስለምንስ ትኲር ብላችሁ ታዩናላችሁ? እኛ በራሳችን ኀይል ወይም በራሳችን መልካም ሥራ ይህን ሰው እንዲራመድ ያደረግነው ይመስላችኋልን?
እናንተ ከዳተኞች! ዓለምን የሚወድ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑን አታውቁምን? እንግዲህ ዓለምን የሚወድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑ ነው።
መልአኩ ግን እንዲህ አለኝ፤ “ስለምን ትደነቃለህ? የሴቲቱን ምሥጢርና እርስዋ የተቀመጠችበትን፥ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች ያሉትን፥ የአውሬውን ምሥጢር እገልጥልሃለሁ፤