Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 16:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ይህን ለእናንተ መናገሬ በእኔ ሆናችሁ ሰላም እንዲኖራችሁ ብዬ ነው፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፥ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 “በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህን ነግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፤”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በእ​ኔም ሰላ​ምን እን​ድ​ታ​ገኙ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ በዓ​ለም ግን መከ​ራን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለ​ሙን ድል ነሥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 16:33
46 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤ ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ።


እርሱም ሰላማቸው ይሆናል። አሦራውያን ምድራችንን ለመውረር ቢመጡና በምሽጎቻችን ላይ ቢወጡ ሰባት ጠባቂዎችንና ስምንት መሪዎችን በእነርሱ ላይ እናስነሣለን።


በዚያም ሰዎች በአልጋ ላይ የተኛ አንድ ሽባ ይዘው ወደ እርሱ መጡ። እርሱም እምነታቸውን አይቶ፥ ሽባውን፥ “ልጄ ሆይ! አይዞህ፤ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።


እንዲህ ይሉም ነበር፤ “በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው! ሰላም በሰማይ፥ ክብርም ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን!”


“በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን! በምድርም እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ሁሉ ሰላም ይሁን!” ይሉ ነበር።


ይህ ዓለም የሚፈረድበት ጊዜ አሁን ነው፤ የዚህ ዓለም ገዢ ሰይጣን ወደ ውጪ የሚጣለው አሁን ነው፤


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም እመኑ፤


“ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዐይነት አይደለም፤ ልባችሁ አይጨነቅ፤ ደግሞም አይፍራ።


ስለ ፍርድ የሚያጋልጠው የዚህ ዓለም ገዢ ስለ ተፈረደበት ነው።


በእነዚያም አገሮች ሁሉ አማኞች በእምነታቸው እንዲጸኑ በማበረታታትና በመምከር “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መከራ መቀበል አለብን” እያሉ አስተማሩአቸው።


በማግስቱ ሌሊት ጌታ በጳውሎስ አጠገብ ቆሞ “አይዞህ በኢየሩሳሌም እንደ መሰከርክልኝ፥ እንዲሁም በሮም ልትመሰክርልኝ ይገባሃል” አለው።


አሁንም መርከቡ ብቻ ይጐዳል እንጂ ከእናንተ በማንም ላይ ጥፋት አይደርስም፤ ስለዚህ አይዞአችሁ፤ አትፍሩ! ብዬ እመክራችኋለሁ።


ስለዚህ እናንተ ሰዎች አይዞአችሁ! እግዚአብሔር ይህንን የነገረኝን ሙሉ በሙሉ እንደሚፈጽም አምነዋለሁ።


በይሁዳ፥ በገሊላና በሰማርያ ሁሉ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሰላም አገኘች፤ በረታችም፤ ጌታን እያከበረችና በመንፈስ ቅዱስ እየተጽናናች በቊጥር አደገች።


ለምሕረት አባትና መጽናናትን ሁሉ ለሚሰጥ እንዲሁም ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አባት ለእግዚአብሔር፥ ምስጋና ይሁን።


በተረፈውስ ወንድሞቼ ሆይ! ደኅና ሁኑ! አኗኗራችሁን አስተካክሉ፤ ምክሬን ተከተሉ፤ እርስ በእርሳችሁ ተስማሙ፤ በሰላምም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።


ነገር ግን እኛን ዘወትር በክርስቶስ ድል አድራጊዎች አድርጎ ለሚመራንና መልካም መዓዛ እንዳለው ሽቶ ስለ ክርስቶስ ያለንን ዕውቀት በየስፍራው ሁሉ እንድናዳርስ ለሚያደርገን አምላክ ምስጋና ይሁን!


ነገር ግን ይህ ከሁሉ የሚበልጠው ኀይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ አለመሆኑ እንዲታወቅ ይህን ክቡር ነገር እንደ ሸክላ ዕቃ ሆነን ይዘነዋል።


ይልቅስ መከራንና ችግርን ጭንቀትንም እየታገሥን እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን በማናቸውም መንገድ እናቀርባለን።


በእናንተ ላይ ያለኝ እምነት ከፍተኛ ነው፤ በእናንተ ላይ ያለኝ ትምክሕት ትልቅ ነው፤ በእናንተም እጽናናለሁ፤ በመከራችን ሁሉ በጣም እደሰታለሁ።


ከዚህ ከክፉ ዘመን ያድነን ዘንድ በአምላካችንና በአባታችን ፈቃድ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ።


ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር በሌላ መመካት ከእኔ ይራቅ፤ በዚህም መስቀል ዓለም ከእኔ ተለይቶአል፤ እኔም ከዓለም ተለይቼአለሁ።


ከሰው ማስተዋል ሁሉ በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አእምሮአችሁን በኢየሱስ ክርስቶስ ይጠብቃል።


በእርሱም አማካይነት በሰማይም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ፤ በመስቀል ላይ በፈሰሰው በልጁ ደምም ሰላምን አደረገ።


እንዲያውም ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ መከራ እንደሚደርስብን አስቀድመን እንነግራችሁ ነበር፤ እንደምታውቁትም መከራው ደርሶብናል፤


ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፥ እኛ የምንገኘው በችግርና በመከራ ውስጥ ቢሆንም እንኳ በእምነታችሁ ምክንያት በእናንተ ተጽናንተናል።


የሰላም ጌታ ራሱ ሁልጊዜ በሁሉም ነገር ሰላምን ይስጣችሁ፤ ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።


የኢየሱስ ክርስቶስ ወገኖች ሆነው መንፈሳዊ ሕይወትን መኖር የሚፈልጉ ሁሉ ስደት ይገጥማቸዋል።


ስለዚህም እርሱ በኃጢአት ከሚገኘው ጊዜያዊ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ።


አብርሃምም ከያዘው ነገር ሁሉ ዐሥራት አውጥቶ ሰጠው፤ የመልከ ጼዴቅ የስሙ ትርጓሜ አንደኛው “የጽድቅ ንጉሥ” ሌላው “የሳሌም ንጉሥ” ወይም “የሰላም ንጉሥ” ማለት ነው።


በዓለም ሁሉ ያሉ ወንድሞቻችሁ ይህን ዐይነት መከራ እንደሚቀበሉ በማወቅ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።


አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን ስላወቃችሁት እጽፍላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ፥ ሰይጣንን ስላሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።


ልጆች ሆይ! እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ፤ በእናንተ ያለው መንፈስ በዓለም ካለው መንፈስ ይበልጣል። ስለዚህ ሐሰተኞች ነቢያትን አሸንፋችኋል።


የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል፤ ዓለምን የምናሸንፈውም በእምነታችን ነው።


እነርሱ በበጉ ደምና በተናገሩት የምስክርነት ቃል ድል ነሥተውታል፤ ለሕይወታቸው ሳይሳሱ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋል፤


እኔ ድል ነሥቼ ከአባቴ ጋር በዙፋኑ ላይ እንደ ተቀመጥኩ እንዲሁም ድል የነሣ ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።


እኔም “ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ” አልኩት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ታላቁን መከራ አልፈው የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ነጭ አድርገውታል፤


ይህንንም ማድረጉ ቀድሞ የጦርነት ልምድ ያልነበራቸውን የእስራኤልን ትውልድ የጦርነት ስልት ለማስተማር ብሎ ብቻ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos