1 ቆሮንቶስ 9:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሩጫ የሚወዳደሩ ሁሉ አድካሚ ልምምድ ያደርጋሉ፤ እነርሱ እንዲህ የሚደክሙት የሚጠፋውንና ጊዜያዊ የሆነውን አክሊል ለማግኘት ነው፤ እኛ ግን የምንደክመው የማይጠፋውንና ዘለዓለማዊ የሆነውን አክሊል ለማግኘት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለውድድር የሚዘጋጅ ማንኛውም ሰው በሁሉም ነገር ራሱን ይገዛል፤ እነርሱ ዐላፊ ጠፊ የሆነውን አክሊል ለማግኘት ይደክማሉ፤ እኛ ግን ለዘላለም የማይጠፋውን አክሊል ለማግኘት እንደክማለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ራሱን መግዛት ይለማመዳል፤ እነርሱ ጠፊውን አክሊል፤ እኛ ግን የማይጠፋውን፥ ለማግኘት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚታገል ሁሉ በሁሉ ነገር ይታገሣል፤ እነርሱስ የሚጠፋውንና የሚያልፈውን የምስጋናቸውን ዋጋ አክሊል ያገኙ ዘንድ ይበረታሉ፤ እኛ ግን የማያልፈውን አክሊል ለማግኘት እንታገሣለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን። |
የእምነትን መልካም ጦርነት ተዋጋ፤ አንተ ወደ እርሱ በተጠራህ ጊዜ በብዙ ምስክሮች ፊት ትክክለኛ ምስክርነትን የሰጠኸውን ዘለዓለማዊውን ሕይወት ያዝ።
ይልቅስ እንግዳ ተቀባይ፥ መልካም የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ ትክክለኛ፥ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ፥ በመጠን የሚኖር ይሁን።
ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ፤ እነሆ፥ እንድትፈተኑ ከእናንተ አንዳንዶቹን ዲያብሎስ ወደ እስር ቤት ያገባችኋል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ፤ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ የሕይወት አክሊል እሰጥሃለሁ።
ኻያ አራቱ ሽማግሌዎች ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚኖረው፥ በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዳሉ፤ አክሊሎቻቸውንም በዙፋኑ ፊት አኑረው፥ እንዲህ ይላሉ፦
እንዲሁም፥ በዙፋኑ ዙሪያ ኻያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸው ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ ኻያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።