ቀጥሎም ከቤትኤል በስተምሥራቅ ወዳለው ተራራማ አገር ወጣ፤ ቤትኤልን በስተምዕራብ፥ ዐይን በስተምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያም መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤
1 ቆሮንቶስ 1:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቆሮንቶስ ከተማ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በውስጥዋም በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱትና ቅዱሳን እንዲሆኑ ለተጠሩት፥ እንደዚሁም በየቦታው ለእነርሱና ለእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ለሚጠሩት ሁሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቆሮንቶስ ላለችው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ተቀድሰው፣ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ሆነው ከሚጠሩት ሁሉ ጋራ ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቆሮንቶስ ሀገር ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለከበሩና ቅዱሳን ለተባሉ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ለሚጠሩ ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፦ |
ቀጥሎም ከቤትኤል በስተምሥራቅ ወዳለው ተራራማ አገር ወጣ፤ ቤትኤልን በስተምዕራብ፥ ዐይን በስተምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያም መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን መላኩ የታወቀ ነው፤ በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰላምን እየሰበከ የመጣውም ለእነርሱ ነው።
ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’
የሰሙትም ሁሉ፥ “ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሁሉ የሚያጠፋ የነበረ አይደለምን? ወደዚህስ የመጣው እነርሱን እያሰረ ወደ ካህናት አለቆች ለመውሰድ አይደለምን?” በማለት ይደነቁ ነበር።
ስለዚህ በሮም ለምትኖሩ፥ እግዚአብሔር ለወደዳችሁና ወገኖቹ እንድትሆኑ ለጠራችሁ ሁሉ፦ ከአባታችን ከእግዚአብሔርና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
እንግዲህ አንዱ ጌታ የሁሉም ጌታ ስለ ሆነ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ምንም ልዩነት የለም፤ እርሱም ለሚለምኑት ሁሉ በረከቱን አብዝቶ ይሰጣል፤
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።
የእኛ አምላክ ግን የሁሉ ነገር ፈጣሪና እኛም የእርሱ የሆንን አንዱ እግዚአብሔር አብ ብቻ ነው፤ እንዲሁም ሁሉ ነገር በእርሱ የተፈጠረና እኛም በእርሱ የምንኖር አንዱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፥ በቆሮንቶስ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንና እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ፥
እኛ የምናስተምረው ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑንና እኛም ራሳችን ስለ ኢየሱስ የእናንተ አገልጋዮች መሆናችንን ነው እንጂ ስለ ራሳችንስ አንሰብክም።
የእግዚአብሔር አብና የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወገኖች ለሆኑ ለተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን፥ ከጳውሎስ፥ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ የተላከ መልእክት ነው፤ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
የእግዚአብሔር የአባታችንና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ለሆነችው ለተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከጳውሎስ፥ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ የተላከ፦
እርሱ እኛ ስላደረግነው መልካም ሥራ ሳይሆን በራሱ ፈቃድና በጸጋው አዳነን፤ ለቅድስናም ጠራን፤ ይህንንም ጸጋ ከዘመናት በፊት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰጠን።
ነገር ግን “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ጸንቶ ይኖራል።
ሰዎችን ቅዱሳን የሚያደርጋቸውና በእርሱ ቅዱሳን የሆኑትም ሰዎች የአንድ አባት ልጆች ናቸው፤ በዚህ ምክንያት ኢየሱስ እነርሱን “ወንድሞቼ” ብሎ ለመጥራት አያፍርም።
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና የያዕቆብ ወንድም ከሆነው ከይሁዳ፥ ለተጠራችሁት፥ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዳችሁት፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለተጠበቃችሁት ሁሉ፥