ማሕልየ መሓልይ 5:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጆቹ የቢረሌ ፈርጥ ያለበት የወርቅ ቀለበት ናቸው፥ አካሉ በሰንፔር ያጌጠ የዝሆን ጥርስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክንዶቹ በቢረሌ ፈርጥ ያጌጠ፣ የወርቅ ዘንግን ይመስላሉ፤ ሰውነቱም በሰንፔር ፈርጥ ያጌጠ፣ አምሮ የተሠራ የዝኆን ጥርስን ይመስላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክንዶቹ የዕንቊ ፈርጥ እንዳለበት የወርቅ ዘንግ ያምራሉ፤ አካሉ በሰንፔር ዕንቊ እንዳጌጠ የዝሆን ጥርስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጆቹ የተርሴስ ፈርጥ እንዳለባቸው እንደ ለዘቡ የወርቅ ቀለበቶች ናቸው፤ ሆዱ በሰንፔር ዕንቍ እንዳጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጆቹ የቢረሌ ፈርጥ እንዳለበት እንደ ወርቅ ቀለበት ናቸው፥ አካሉ ብልሃተኛ እንደ ሠራው በሰንፔር እንዳጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው። |
የመንኰራኵሩም መልክና አሠራር የቢረሌ መልክ ይመስል ነበር፥ የአራቱም መልክ አንድ ዓይነት ነበር፥ መልካቸውና አሠራራቸው በመንኰራኵር መካከል ያለ መንኰራኵር ይመስል ነበር።