Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤ በእስራኤልም ላይ ወደቀ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ለንጉሣዊ ሥልጣኑ ወሰን የለውም፤ መንግሥቱም ዘለዓለማዊ ሰላም የሰፈነበት ይሆናል፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፥ እውነትና ፍትሕ የሰፈነበት መንግሥት በዳዊት ዙፋን ላይ ተመሥርቶ እንዲጸና ያደርገዋል፤ የሠራዊት አምላክ ቅናት ይህን ለማድረግ ወስኖአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ለአ​ለ​ቆች ሰላ​ምን ለእ​ር​ሱም ሕይ​ወ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ በፍ​ር​ድና በጽ​ድቅ ያጸ​ና​ውና ይደ​ግ​ፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆ​ናል፤ በዳ​ዊት ዙፋን መን​ግ​ሥቱ ትጸ​ና​ለች፤ ለሰ​ላ​ሙም ፍጻሜ የለ​ውም። የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ይህን ያደ​ር​ጋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 9:7
34 Referencias Cruzadas  

ቤትህና መንግሥትህ በፊቴ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ ዙፋንህም ለዘለዓለም የጸና ይሆናል።’ ”


ከኢየሩሳሌምና ከጽዮን ተራራ የተረፉት ወገኖች ይወጣሉ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ከመፈጸም አይመለስም።”


ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።


ከእሴይ ግንድ ቁጥቋጥ ይወጣል፤ ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።


ዙፋኑም በምሕረት ይቀናል፥ በዚያም በዳዊት ድንኳን ፍትህን የሚሻ ትክክል የሆነውን ለመፈጸም የሚፈጥን ፈራጅ በእውነት ይቀመጣል።


እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።


አቤቱ ጌታ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች።


ከኢየሩሳሌም ቅሬታ፥ ከጽዮን ተራራ ያመለጡት ይመጣሉ፤ የሠራዊት ጌታ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።


እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይመጣል ክንዱም ስለ እርሱ ይገዛል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደመወዙም በፊቱ ነው።


ጌታ እንደ ኃያል ይወጣል እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፤ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል በጠላቶቹም ላይ ይበረታል።


“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።


የዚህ የኋለኛው ቤት ክብር ከፊተኛው ይልቅ ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” ትርጉሙም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” ማለት ነው።


እንዲህ ሕዝቡ “እኛስ ክርስቶስ ለዘለዓለም እንዲኖር ከሕጉ ሰምተናል፤ አንተስ የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ እንዲያስፈልገው እንዴት ትላላህ? ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለሱለት።


ስለ ልጁ ግን፥ “አምላክ ሆይ! ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የጽድቅ በትር የመንግሥትህ በትር ነው።


እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤


ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም ነጭ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos