ማሕልየ መሓልይ 7:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እንብርትሽ የወይን ጠጅ እንደማይጐድልበት እንደ ተነጠጠ ጽዋ ነው፥ ሆድሽ እንደ ስንዴ ክምር፥ በአበባም እንደ ታጠረ ነው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ዕንብርትሽ ጥሩ የወይን ጠጅ እንደማይጐድልበት፣ እንደ ክብ ጽዋ ነው፤ ወገብሽ ዙሪያውን በውብ አበባ የታሰረ፣ የስንዴ ክምር ይመስላል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እንብርትሽ በወይን ጠጅ የተሞላ ብርሌ ይመስላል፤ ወገብሽ ዙሪያውን በውብ አበባ የታሰረ የስንዴ ነዶ ይመስላል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 አንቺ የአሚናዳብ ልጅ ሆይ፥ በጫማ አካሄድሽ እጅግ ያማረ ነው። የዳሌዎችሽ አቀማመጥ በአንጥረኛ እጅ እንደ ተሠሩ እንደ ዕንቍዎች ይመስላል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 አንቺ የመኰንን ልጅ ሆይ፥ እግሮችሽ በጫማ ውስጥ እንዴት ውቦች ናቸው! ዳሌዎችሽስ በአንጥረኛ እጅ እንደ ተሠሩ እንደ ዕንቍዎች ይመስላሉ። Ver Capítulo |