ሮሜ 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመልካም ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘለዓለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጎ የሆነውን ጸንቶ በማድረግ ክብርን፣ ሞገስንና ዘላለማዊነትን ለሚሹ የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመልካም ሥራ በመጽናት ምስጋናና ክብርን የማይጠፋ ሕይወትንም ለሚፈልጉ እግዚአብሔር የዘለዓለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበጎ ምግባር ጸንተው ለሚታገሡ፥ ምስጋናና ክብርን፥ የማይጠፋ ሕይወትንም ለሚሹ እርሱ የዘለዓለም ሕይወትን ይሰጣቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበጎ ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤ |
ድሀ ከመበደል እጁን ቢመልስ፥ አራጣ ወይም ትርፍ ባይወስድ፥ ፍርዴን ቢያደርግ፥ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኃጢአት አይሞትም።
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።
ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለጠግነት ምን እንደሆነ ሊያሳውቅ ወደደ፤ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ያለው ክርስቶስ ነው።
አሁን ግን በወንጌል አማካይነት ሞትን በሻረው፥ ሕይወትንና ያለመበስበስን ወደ ብርሃን ባመጣው በአዳኛችን በክርስቶስ ኢየሱስ መገለጥ በኩል ተገለጠ።