መዝሙር 92:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፥ ዓመፃንም የሚሠሩ ሁሉ ይበተናሉና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእኔን ቀንድ ግን እንደ አውራሪስ ቀንድ ከፍ ከፍ አደረግኸው፤ በለጋ ዘይትም አረሰረስኸኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ እንደ ጐሽ ቀንድ ከፍ አደረግኸኝ፤ በትኲስ ዘይትም ቀባኸኝ። |
እግዚአብሔርም ከግብጽ አውጥቶታል፤ ጉልበቱ አንደ ጎሽ ቀንድ ያለ ነው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፥ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፥ በፍላጾቹም ይወጋቸዋል።
አቤቱ፥ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፥ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኃይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፥ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።
ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፦ “ልቤ በጌታ ደስ ይለዋል፥ ቀንዴም በጌታ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛልና፥ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ።
ጌታ! እርሱን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፥ ከሰማይም ያንጐደጉድባቸዋል፥ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሢሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”