Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 24:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እግዚአብሔርም ከግብጽ አውጥቶታል፤ ጉልበቱ አንደ ጎሽ ቀንድ ያለ ነው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፥ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፥ በፍላጾቹም ይወጋቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤ ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው፤ ጠላቶች የሆኗቸውን ሕዝብ ያነክታሉ፤ ዐጥንቶቻቸውን ያደቅቃሉ፤ በፍላጾቻቸው ይወጓቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከግብጽ ያወጣቸው እግዚአብሔር ለእነርሱ እንደ ጐሽ ይዋጋላቸዋል፤ ጠላቶቻቸው የሆኑትን ሕዝቦች ይቦጫጭቅላቸዋል፤ አጥንቶቻቸውን ያደቃል፤ ቀስቶቻቸውንም ይሰባብራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ መርቶ አው​ጥ​ቶ​ታል፤ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ክብር አለው፤ ጠላ​ቶ​ቹን አሕ​ዛ​ብን ይበ​ላል፤ አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ባ​ብ​ራል፤ በፍ​ላ​ጾ​ቹም ጠላ​ቱን ይወ​ጋ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግዚአብሔርም ከግብፅ አውጥቶታል፤ ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ነው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፥ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፥ በፍላጾቹም ይወጋቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 24:8
18 Referencias Cruzadas  

ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም አቅና ተከናወን ንገሥም፥ ቀኝህም በክብር ይመራሃል።


እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።


በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ታደቃቸዋለህ።


እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ብድግ ይላል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አያርፍም።”


ከግብጽ ያወጣቸው እግዚአብሔር፥ ለእነርሱ እንደ ጎሽ ቀንድ ያለ ነው።


ብቻ፥ በጌታ ላይ አታምፁ፤ ለእኛ እንደ እንጀራ ቁራሽ ናቸውና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ ጌታም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው።”


እነሆ፥ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አስነሣለሁ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ፤ በእርሷም ላይ ይሰለፋሉ፥ ከዚያም ትያዛለች፤ ፍላጾቻቸውም ተጨናግፎ ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ብልህ ጀግና ፍላጻ ናቸው።


እስኪ ነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፤ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፤ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ፍጻሜዬን አቀረብከው።


ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥ የማይቻላቸውንም ምክር አሰቡ።


ከተገደሉት ደም፥ ከተማረኩትም ደም፥ ከጠላት አለቆችም ራስ፥ ፍላጾቼን በደም አሰክራለሁ፥ ሰይፌም ሥጋ ይቆራርጣል።”


“‘በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ፤ ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ።


“ጌታ አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከአንተ የበለጡትን እና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ፥ ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን ባስወጣልህ ጊዜ፥


ሕዝቡም በጌታና በሙሴ ላይ እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? እንጀራ የለም፥ ውኃም የለም፤ ሰውነታችንም ይህን የሚያንገሸግሽ እንጀራ ተጸየፈ።”


ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ፥ ይህም ከጌታ ዘንድ በነቢይ “ልጄን ከግብጽ ጠራሁት” የተባለው እንዲፈጸም ነው።


ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ ጌታ የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።


አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጠላለሁ፥ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ።


ኃያል ሆይ፥ ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፥ እነርሱም በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ፥ አሕዛብም በበታችህ ይወድቃሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios