ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
መዝሙር 8:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤ ክብርንና ግርማን አጐናጸፍኸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመላእክት በጥቂቱ ብታሳንሰውም፥ የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንክለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመላእክት ጥቂት አሳነስኸው፤ በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው። |
ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
ከዚያም አቤሴሎም ወደ ንጉሡ እንዲሄድለት ኢዮአብን አስጠራው፤ ኢዮአብ ግን ወደ እርሱ አልመጣም፤ ለሁለተኛ ጊዜም ላከበት፤ ኢዮአብ ግን አሁንም ሳይመጣ ቀረ።
የተቀመጠውም ከግዛትና ከሥልጣን፥ ከኃይልና ከጌትነት እንዲሁም በዚህ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ ነው።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞትን እንዲቀምስ፥ ከመላእክት ለጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖ ኢየሱስን እናየዋለን።