መዝሙር 51:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፤ አዲስና የጸና መንፈስን ስጠኝ። |
አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የአመንዝራነትሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ፥ በሜዳም አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?”
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አሁንም የእስራኤል ቤት እንድሠራላቸው እንዲፈልጉኝ እፈቅድላቸዋለሁ፥ ሰዎችንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።
መልካም፥ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።