La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 137:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉአትን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ሆይ፤ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን፣ ኤዶማውያን እንዴት እንደ ዛቱ ዐስብ፤ ደግሞም፣ “አፍርሷት፤ ፈጽማችሁ አፈራርሷት!” አሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሆይ! ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ቀን ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፤ “እስከ መሠረትዋ አፈራርሳችሁ ጣሉአት!” እያሉ መጮኻቸውንም አስታውስ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በመ​ከራ መካ​ከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድ​ነ​ኛ​ለህ፤ በጠ​ላ​ቶች ቍጣ ላይ እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፥ ቀኝ​ህም ያድ​ነ​ኛል

Ver Capítulo



መዝሙር 137:7
17 Referencias Cruzadas  

አምላኬ ሆይ፥ ጦቢያን፥ ሰንባላጥን ስለዚህ ሥራቸው ደግሞም ሊያስፈራሩኝ ነቢያቱን ኖዓድያና የተቀሩት ነቢያትን አስብ።


ይህንንም አስታውስ፥ ጠላት በጌታ ተሳለቀ፥ አላዋቂ ሕዝብም በስምህ ቀለደ።


ጌታም ሙሴን፦ “ይህንን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ አኑረው፥ የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና” አለው።


የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በመሆኑ እንደተደሰትህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፤ የሴይር ተራራ ሆይ፥ አንተ፥ ኤዶም ሁሉና ሁለንተናዋ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርበት፥


እኔም ክፋታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ ልብ አላደረጉም፤ አሁንም ሥራዎቻቸው ከብበዋቸዋል፥ እነርሱም በፊቴ አሉ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ ርኅራኄውንም ሁሉ አጥፍቷልና፥ ባለማቋረጥም ተቆጥቷልና፥ መዓቱንም ለዘለዓለም ጠብቆአልና ስለ ሦስት የኤዶምያስ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።


ሕዝብህን ለመታደግ፥ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፤ የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፥ ከመሠረቱ እስከ አንገቱ ድረስ አራቆትህ።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ ስለ ተቃወሙት እቀጣቸዋለሁ።