እርሱ፥ እንደ ንጋት ብርሃን እንደ ማለዳ ፀሐይ አወጣጥ፥ ደመና በሌለበት ማለዳ እንደምታበራ የብርሃን ጸዳል፥ ከዝናብ በኋላ ከምድር እንደሚበቅል ልምላሜ ይሆናል።
ምሳሌ 4:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ ብርሃኑ እየጐላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደጋግ ሰዎች መንገድ እንደ ንጋት ብርሃን ነው፤ የቀኑ ሙሉ ብርሃን እስኪሆን ድረስ ብርሃኑ እየጨመረ ይሄዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጻድቃን መንገዶች ግን እንደ ብርሃን ይበራሉ። ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየጨመሩ ይበራሉ። |
እርሱ፥ እንደ ንጋት ብርሃን እንደ ማለዳ ፀሐይ አወጣጥ፥ ደመና በሌለበት ማለዳ እንደምታበራ የብርሃን ጸዳል፥ ከዝናብ በኋላ ከምድር እንደሚበቅል ልምላሜ ይሆናል።
እኛም እንወቅ፤ ጌታን ለማወቅ እንትጋ፤ እንደ ንጋትም መገለጡ እርግጥ ነው፤ እንደ ዝናብ ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ በልግ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”
ይህን በማድረግ በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች እንድትሆኑ ነው፤ እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣልና፥ ለጻድቃንና ለኃጥኣንም ዝናቡን ያዘንባልና።
እኛም ሁላችን፥ በመጋረጃ በማይሸፈን ፊት፥ የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን፥ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፥ ይህም መንፈስ ከሚሆን ጌታ የመጣ ነው።
በዚህም በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ሆናችሁ በዚህ ዓለም እንደ ከዋክብት የምታበሩ፥ ያለ ነቀፋ የዋሆችና ነውርም የሌለባችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ፤
ደግሞም ይህን የበለጠ የሚያረጋግጥ የነቢያት ቃል አለ፤ ጎሕ እስኪቀድ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪገለጥ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚያስተውል ቃሉን ልብ በማለት መልካም ታደርጋላችሁ።
ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።
አቤቱ፥ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፥ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኃይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፥ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።