የኀጥኣን ቤት ይፈርሳል፥ የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል።
የክፉዎች ቤት ይፈርሳል፤ የቅኖች ድንኳን ግን ይስፋፋል።
የክፉ ሰው ቤት ይፈርሳል፤ የደግ ሰው ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።
የክፉዎች ቤቶች ይፈርሳሉ፤ የቅኖች ማደሪያዎች ግን ይጸናሉ።
የአምላክ አልባ ሰው ጉባኤ ፍሬ የለውም፥ የጉቦ ድንኳኖችንም እሳት ትበላለች።
በእውነት የኃጢአተኞች ቤት እንዲሁ ናት፥ እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው ስፍራ ይህ ነው።”
እናንተ፦ የከበርቴው ቤት የት ነው? ክፉዎች ያደሩበት ድንኳን የት ነው? ብላችኋል።
ቤቱን ይደገፈዋል፥ ነገር ግን አይቆምለትም፥ ይይዘውማል፥ አይጸናለትም።
የሚጠሉህ ኃፍረት ይከናነባሉ፥ የክፉዎችም ድንኳን አይገኝም።”
ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት እርሱ አንተን ነቅቶ ይጠብቅሃል፥ የጽድቅህንም መኖሪያ ያረጋግጥልሃል።
ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፥ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።
ጥቂት ጊዜ ቆይቶ፥ ክፉ አድራጊ አይኖርም፥ ትፈልገዋለህ ቦታውንም አታገኝም።
በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፥ ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ።
ክፉ ሰዎች ይወድቃሉ፥ ፈጽሞም አይገኙም፥ የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።
ጌታ የትዕቢተኞችን ቤት ይነቅላል፥ የባልቴትን ዳርቻ ግን ያጸናል።
ጻድቅ ስለ ኀጥእ ቤት ያስባል፥ ኀጥኣንም ለጥፋት እንደ ተገለበጡ።
የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፥ አእምሮ የሌለው ሰው ግን ያሟጥጠዋል።
የጌታ መርገም በክፉ ሰዎች ቤት ነው፥ የጻድቃን ቤት ግን ይባረካል።
እኔ እልከዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ ወደሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፤ በቤታቸውም ውስጥ ይኖራል፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።”