Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 18:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በእውነት የኃጢአተኞች ቤት እንዲሁ ናት፥ እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው ስፍራ ይህ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በርግጥ የክፉ ሰው መኖሪያ፣ እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው መድረሻ ይህ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ምን ጊዜም የክፉ ሰዎች መጨረሻ ይኸው ነው፤ እግዚአብሔርንም የማይፈሩ ሰዎች ዕድል ፈንታቸው ይህ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ቤት እን​ዲህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የማ​ያ​ውቁ ሰዎች ስፍራ ይህ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በእውነት የኃጢአተኞች ቤት እንዲሁ ናት፥ እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው ስፍራ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 18:21
16 Referencias Cruzadas  

ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።


እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ በግልጥ ይናገራሉ ዳሩ ግን በሥራቸው ይክዱታል፤ የሚያጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ ብቁ ያልሆኑ ናቸው።


ነገር ግን እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤


ይህን ስታደርጉ ግን እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት መሆን የለበትም፤


ያዕቆብን በልተውታልና፥ ውጠውታልምና፥ አጥፍተውታልምና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አውርድ።


ያ ሁሉ ትውልድ ወደ አባቶቹ ከተከማቸ በኋላ ጌታንም ሆነ እርሱ ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ነገር የማያውቅ ሌላ ትውልድ ተነሣ።


እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈለጉ እግዚአብሔር ተገቢ ያልሆነውን ነገር እንዲያደርጉ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤


በማያውቁህ አሕዛብ ላይ፥ ስምህንም በማይጠሩ መንግሥታት ላይ መዓትህን አፍስስ፥


እናንተ፦ የከበርቴው ቤት የት ነው? ክፉዎች ያደሩበት ድንኳን የት ነው? ብላችኋል።


እግዚአብሔርንም፦ “ከእኛ ዘንድ ራቅ፥ መንገድህን እናውቅ ዘንድ አንወድድም።


“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።


የዔሊም ልጆች ለጌታ ክብር የማይሰጡ ስድ አደጎች ነበሩ።


ፈርዖንም፦ “ቃሉን እንድሰማ እስራኤልንስ እንድለቅ ጌታ ማን ነው? ጌታን አላውቅም፥ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም” አለ።


ገመዳቸው የተነቀለ አይደለምን? አለጥበብም ይሞታሉ።’”


ኢዮብም መለሰ፤ እንዲህም አለ፦


ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥ ከአምላክ የተመደበለት ርስቱ ይህ ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios