La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 22:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ብዙም ስለ ነበሩ ሞዓብ ሕዝቡን እጅግ ፈራ፤ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ሞዓብ ደነገጠ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሞዓብም ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ተሸበረ፤ በርግጥም ሞዓብ በእስራኤላውያን ምክንያት በፍርሀት ተውጦ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በእስራኤላውያን ብዛት ምክንያት የሞአብ ሕዝብ ታላቅ ፍርሀት ዐደረባቸው፤ እስራኤላውያንንም በጣም ፈሩ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብዙም ነበ​ረና ሞዓብ ከሕ​ዝቡ እጅግ ፈራ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ ሞዓብ ደነ​ገጠ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ብዙም ነበረና ሞዓብ ከሕዝቡ እጅግ ፈራ፤ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ሞዓብ ደነገጠ።

Ver Capítulo



ዘኍል 22:3
10 Referencias Cruzadas  

ይህም ደግሞ የእስራኤልን ልጆች በምግብና በውኃ ስላልተቀበሉአቸውና እንዲረግማቸውም በለዓምን ስለ ገዙት ነው፤ ነገር ግን አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው።


እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉ ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።


ነገር ግን በጨቆኑአቸው መጠን እንዲሁ በዙ፥ እጅግም ሰፉ፤ ከዚህም የተነሣ እስራኤላውያንን ፈሩአቸው።


የዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ደነገጡ፤ የሞዓብ መሪዎች መንቀጥቀጥ ያዛቸው፤ በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ።


መፈራቴን በፊትህ እልካለሁ፥ የምትሄድበትን ሕዝብ ሁሉ አስደንግጣቸዋለሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ በፊትህ ጀርባቸውን እንዲያዞሩ አደርጋለሁ።


ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፤ በግብጽ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል።


ከሰማይ በታች ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን ማኖር ዛሬ እጀምራለሁ፥ ወሬህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፥ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።’”


ኢያሱንም እንዲህ አሉት፦ “በእውነት ጌታ አገሩን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአል፤ ከእኛም የተነሣ በአገሩ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በፍርሃት ቀልጠዋል።”


መልሰውም ኢያሱን እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ በእርሷም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ እንዲያጠፋ ጌታ አምላክህ ባርያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፥ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ስለ ፈራን ይህን ነገር አድርገናል።