Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 13:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ይህም ደግሞ የእስራኤልን ልጆች በምግብና በውኃ ስላልተቀበሉአቸውና እንዲረግማቸውም በለዓምን ስለ ገዙት ነው፤ ነገር ግን አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ይህ የሆነው እስራኤልን በምግብና ውሃ መስተንግዶ በመቀበል ፈንታ፣ በለዓም እንዲረግምላቸው በገንዘብ ስለ ገዙት ነበር። ይሁን እንጂ አምላካችን ርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ይህም ትእዛዝ የተሰጠበት ምክንያት እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡበት ጊዜ በጒዞ ላይ ሳሉ ሞአባውያንና ዐሞናውያን ምግብና ውሃ ስለ ከለከሉአቸው ነበር፤ ይልቁንም ይህን በማድረግ ፈንታ ለበለዓም ገንዘብ ሰጥተው የእስራኤልን ሕዝብ እንዲረግምላቸው አድርገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን መርገሙን ወደ በረከት ለወጠው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእ​ን​ጀ​ራና በውኃ አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ቸ​ው​ምና፥ ይረ​ግ​ማ​ቸ​ውም ዘንድ በለ​ዓ​ምን ገዝ​ተ​ው​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤ ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችን ርግ​ማ​ኑን ወደ በረ​ከት መለ​ሰው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የእስራኤልን ልጆች በእንጀራና በውኃ ስላልተቀበሉአቸውና ይረግማቸው ዘንድ በለዓምን ስለ ገዙባቸው ነው፥ ነገር ግን አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት መለሰው።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 13:2
12 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር በለዓምን መስማት አልፈለገም፥ ጌታ እግዚአብሔር ወድዶሃልና እርግማኑን በረከት አደረገልህ።


ንጉሡም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው።’


ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያቀደውን፥ የቤዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትን፥ የጌታን ጽድቅ እንድታውቅ ከሺጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ የሆነውን እባክህን አስታውስ።


እነርሱ ይራገማሉ አንተ ግን ትባርካለህ፥ በእኔ ላይ የሚነሡ ይፈሩ፥ አገልጋይህ ግን ደስ ይበለው።


በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ሆይ! ተነሣ፥ ስማም፤ የሴፎር ልጅ ሆይ! አድምጠኝ፤


እነርሱ የቀናውን መንገድ ትተው ተሳሳቱ፤ ክፉ በመሥራት የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከተሉ፤


“አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፥ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳን ቢሆን ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ።


ምክንያቱም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዝተውት ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios