Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 22:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ብዙም ነበ​ረና ሞዓብ ከሕ​ዝቡ እጅግ ፈራ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ ሞዓብ ደነ​ገጠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሞዓብም ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ተሸበረ፤ በርግጥም ሞዓብ በእስራኤላውያን ምክንያት በፍርሀት ተውጦ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ብዙም ስለ ነበሩ ሞዓብ ሕዝቡን እጅግ ፈራ፤ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ሞዓብ ደነገጠ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በእስራኤላውያን ብዛት ምክንያት የሞአብ ሕዝብ ታላቅ ፍርሀት ዐደረባቸው፤ እስራኤላውያንንም በጣም ፈሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ብዙም ነበረና ሞዓብ ከሕዝቡ እጅግ ፈራ፤ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ሞዓብ ደነገጠ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 22:3
10 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእ​ን​ጀ​ራና በውኃ አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ቸ​ው​ምና፥ ይረ​ግ​ማ​ቸ​ውም ዘንድ በለ​ዓ​ምን ገዝ​ተ​ው​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤ ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችን ርግ​ማ​ኑን ወደ በረ​ከት መለ​ሰው።


ክፋ​ትን ወደ ጠላ​ቶች ይመ​ል​ሳ​ታል፤ በእ​ው​ነ​ት​ህም አጥ​ፋ​ቸው።


ነገር ግን እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው መጠን እን​ዲሁ በዙ፤ እጅ​ግም ጸኑ ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ይጸ​የ​ፉ​አ​ቸው ነበር።


ያን ጊዜ የኤ​ዶም አለ​ቆች ሸሹ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች መን​ቀ​ጠ​ቀጥ ያዛ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን የሚ​ኖሩ ሁሉ ቀለጡ።


በፊ​ትህ መፈ​ራ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የም​ት​ሄ​ድ​በ​ትን ሕዝብ ሁሉ አስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም ሁሉ እን​ዲ​ሸ​ሹ​ልህ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ወሬዋ ወደ ግብፅ በደ​ረሰ ጊዜ ስለ ጢሮስ ምጥ ይይ​ዛ​ቸ​ዋል።


ከሰ​ማይ በታች ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ማስ​ደ​ን​ገ​ጥ​ህ​ንና ማስ​ፈ​ራ​ት​ህን እሰ​ድድ ዘንድ ዛሬ እጀ​ም​ራ​ለሁ፤ ስም​ህን በሰሙ ጊዜ በፊ​ትህ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ድን​ጋ​ጤም ይይ​ዛ​ቸ​ዋል።


ኢያ​ሱ​ንም፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሀገ​ሩን ሁሉ በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አል፤ በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ከእኛ የተ​ነሣ ደነ​ገጡ” አሉት።


መል​ሰ​ውም ኢያ​ሱን፥ “እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ ያጠፋ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ውን ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ በእ​ው​ነት ሰም​ተ​ናል፤ ስለ​ዚ​ህም ከእ​ና​ንተ የተ​ነሣ ስለ ነፍ​ሳ​ችን እጅግ ፈራን፤ ይህ​ንም ነገር አድ​ር​ገ​ናል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos