Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 23:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 መፈራቴን በፊትህ እልካለሁ፥ የምትሄድበትን ሕዝብ ሁሉ አስደንግጣቸዋለሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ በፊትህ ጀርባቸውን እንዲያዞሩ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 “በሚያጋጥሙህ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስፈራቴን በፊትህ እልካለሁ፤ ግራም አጋባቸዋለሁ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ወደ ኋላ ተመልሰው እንዲሸሹ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 “አንተን የሚቃወሙህ ሁሉ እኔን እንዲፈሩ አደርጋለሁ፤ በአንተ ላይ ጦርነት በሚያስነሡ ሕዝቦች ላይ ሁከት አመጣለሁ፤ ጠላቶችህ ወደ ኋላ ተመልሰው እንዲሸሹ አደርጋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በፊ​ትህ መፈ​ራ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የም​ት​ሄ​ድ​በ​ትን ሕዝብ ሁሉ አስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም ሁሉ እን​ዲ​ሸ​ሹ​ልህ አደ​ር​ጋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 መፈራቴንም በፊትህ እሰድዳለሁ፥ የምትሄድበትንም ሕዝብ ሁሉ አስደንግጣቸዋለሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ በፊትህ ጀርባቸውን እንዲያዞሩ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 23:27
17 Referencias Cruzadas  

ከሰማይ በታች ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን ማኖር ዛሬ እጀምራለሁ፥ ወሬህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፥ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።’”


ተነሥተውም ሄዱ፥ የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፥ የያዕቆብንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም።


ጌታ አምላካችሁ ግን እነርሱን በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ እስኪጠፉም ድረስ በታላቅ ሁከት ላይ ይጥላቸዋል።


ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም፤ ጌታ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማስደንገጣችሁንና መፈራታችሁን በምትሄዱበት በየትኛውም ምድር ሁሉ ላይ ያሳድራል።”


ለጦርነት ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ።


ከጌታም ዘንድ ታላቅ ድንጋጤ ስለ ያዛቸው በጌራራ ዙሪያ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ ድል በማድረግ በከተሞቹም ውስጥ እጅግ ብዝበዛ ነበርና ከተሞቹን ሁሉ በዘበዙ።


ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር።


በሰፈር በእርሻ ላይና በሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ሆነ፤ ከተማ ጠባቂዎችና አደጋ ጣዮችም ሁሉ ተቀጠቀጡ፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ሽብሩም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነበር።


ከዚያም ጌታ እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል፤ እናንተም፥ ከእናንተ ይልቅ ታላላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ታስለቅቃላችሁ።


በፊትህ መልአክ እልካለሁ፥ ከነዓናዊውን፥ አሞራዊውን፥ ኬጢያዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን አወጣልሃለሁ።


የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው።


ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥ የማይቻላቸውንም ምክር አሰቡ።


አሕዛብን ከፊትህ አስወግዳለሁ፥ ድንበርህንም አሰፋለሁ፤ በጌታ አምላክህ ፊት ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም።


ብዙም ስለ ነበሩ ሞዓብ ሕዝቡን እጅግ ፈራ፤ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ሞዓብ ደነገጠ።


ይህም፥ ጌታ እንደሰጠህ ተስፋ፥ ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ በማሳድድ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios