ከዚህ በኋላ በዳዊት ከተማ በስተ ውጭው ከግዮን ምዕራብ በሸለቆው ውስጥ እስከ ዓሳ በር መግቢያ ድረስ ቅጥር ሠራ። በዖፌልም አዞረበት፥ እጅግም ከፍ አደረገው፤ በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ የጭፍራ አለቆችን አኖረ።
ነህምያ 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የስናአ ልጆች “የዓሣ በር” ሠሩ፤ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ በሮቹን አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዓሣ በሩን የሃስናአ ልጆች ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ መቀርቀሪያዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሃስናአ ጐሣ አባሎች የዓሣ ቅጽር በር የተባለውን ሠሩ፤ ምሰሶዎችንም አቆሙለት፤ በሮችንም ገጠሙ፤ ለበሮቹም መዝጊያ፥ መወርወሪያና ቊልፎችን አበጁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአስናሃ ልጆችም የዓሣ በር ሠሩ፤ ሠረገሎቹንም አኖሩ፤ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሃስናአ ልጆችም የዓሣ በር ሠሩ፥ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ። |
ከዚህ በኋላ በዳዊት ከተማ በስተ ውጭው ከግዮን ምዕራብ በሸለቆው ውስጥ እስከ ዓሳ በር መግቢያ ድረስ ቅጥር ሠራ። በዖፌልም አዞረበት፥ እጅግም ከፍ አደረገው፤ በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ የጭፍራ አለቆችን አኖረ።
ከ “ኤፍሬም በር” በላይ፥ ከ “አሮጌው በር” በላይ፥ በ “ዓሣ በር” በ “ሐናንኤል ግንብ”፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፥ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።
ለንጉሡ ደን ጠባቂ ለአሳፍ በቤቱ አጠገብ ላለው ምሽግ በሮች፥ ለከተማው ቅጥር፥ ለምገባበትም ቤት እንጨት እንዲሰጠኝ ደብዳቤ ይሰጠኝ” አልኩት። ንጉሡም በእኔ ላይ እንዳለችው እንደ አምላኬ መልካም እጅ ሰጠኝ።
በአጠገባቸውም የቆጽ ልጅ የኡሪያ ልጅ ሜሬሞት አደሰ። በአጠገባቸውም የመሼዛቤል ልጅ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም አደሰ። በአጠገባቸውም የባዓና ልጅ ጻዶቅ አደሰ።
እንዲህም ሆነ ምንም እንኳ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በበሮቹ ውስጥ ሳንቃዎቹን ባልገጥምም ቅጥሩን እንደሠራሁ፥ አንድም የፈረሰ እንዳልቀረ ሰንባላጥ፥ ጦቢያና ዓረባዊው ጌሼም የቀሩትም ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፥