ከሌዋውያንም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን እነዚህ ናቸው፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረና ያለ ሌላ ሥራ በየእልፍኛቸው ይቀመጡ ነበር።
ነህምያ 12:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀድሞ በዳዊትና በአሳፍ ዘመን ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን የውዳሴ መዝሙሮችና ምስጋና የሚመሩ የመዘምራን አለቆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከንጉሥ ዳዊትና የመዘምራን አለቃ ከነበረው አሳፍ ዘመንም ጀምሮ ለመዘምራንና ለማኅሌታዊ ዜማ መሪዎች ነበሩአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዳዊትም ዘመን አሳፍ የመዘምራን አለቃ ነበር፤ እነርሱም እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ። |
ከሌዋውያንም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን እነዚህ ናቸው፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረና ያለ ሌላ ሥራ በየእልፍኛቸው ይቀመጡ ነበር።
ንጉሡም ሕዝቅያስና ሹማምንቱ ሌዋውያንን በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ ቃል ጌታን እንዲያመሰግኑ አዘዙ። በደስታም እያመሰገኑ፥ አጐነበሱም ሰገዱም።
ምስጋናውን በጸሎት ለመጀመር መሪ የነበረው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፤ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የነበረው ባቅቡቅያ፤ የይዱቱን ልጅ፥ የጋላል ልጅ፥ የሻሙዓ ልጅ ዓብዳ።