ነህምያ 11:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ምስጋናውን በጸሎት ለመጀመር መሪ የነበረው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፤ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የነበረው ባቅቡቅያ፤ የይዱቱን ልጅ፥ የጋላል ልጅ፥ የሻሙዓ ልጅ ዓብዳ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በምስጋናና በጸሎት ጊዜ ይመራ የነበረው የዋናው አለቃ የአሳፍ ልጅ፣ የዘብዲ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ፣ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የሆነው በቅቡቅያ፣ የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሳሙስ ልጅ አብድያ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ማታንያ የሚካ ልጅ፥ የዘብዲ ልጅ፥ የመዘምራን አለቃ የነበረው የአሳፍ ልጅ፥ የእርሱ ምክትል የነበረው የባቅቡቅያ ልጅና፥ የሻሙዐ ልጅ የነበረው ዐብዳ፥ የጋላል ልጅ፥ የዩዱቱን ልጅ፥ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚጀምሩ አለቃው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ ቦቂቦቅያ፥ የኢዶትም ልጅ፥ የጌላል ልጅ፥ የሰሙዓ ልጅ አብድያ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚቀነቅኑ አለቃው የአሳፍ ልጅ የዘብዲ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ በቅበቃር፥ የኤዶታምም ልጅ የጋላል ልጅ የሳሙስ ልጅ አብድያ። Ver Capítulo |