ደግሞም የተቀደሰ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም፥ ለእህል ቁርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በመለክያ ሁሉ ያገልግሉ ነበር።
ዘሌዋውያን 6:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እርሱ በተቀባበት ቀን የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ ክፍል መልካሙን ዱቄት እኩሌታውን በጥዋት፥ እኩሌታውንም በማታ ለዘወትር የእህል ቁርባን አድርገው ለጌታ የሚያቀርቡት የአሮንና የልጆቹ ቁርባን ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሮን ወይም ልጆቹ በተቀቡበት ዕለት ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ቍርባን ይህ ነው፦ የኢፍ አንድ ዐሥረኛው የላመ ዱቄት ግማሹን ለጧት፣ ግማሹን ለማታ የዘወትር የእህል ቍርባን አድርገው ያቅርቡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ካህኑ በሚሾምበት ቀን መጠኑ በየዕለቱ ከሚቀርበው የእህል መባ ጋር እኩል የሆነ አንድ ኪሎ የላመ ዱቄት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ ያምጣ፤ እርሱም ከፊሉ ጠዋት፥ ከፊሉ ደግሞ ማታ መሥዋዕት ሆኖ ይቅረብ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እርሱን በቀባህበት ቀን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት የአሮንና የልጆቹ መባ ይህ ነው። የኢፍ መስፈርያ ዐሥረኛ ክፍል መልካሙን ዱቄት እኩሌታውን በጥዋት፥ እኩሌታውንም በማታ ለዘወትር መሥዋዕት ያቀርባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተቀቡበት ቀን የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ ክፍል መልካሙን ዱቄት እኵሌታውን በጥዋት፥ እኵሌታውንም በማታ ለዘወትር የእህል ቍርባን አድርገው ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት የአሮንና የልጆቹ ቍርባን ይህ ነው። |
ደግሞም የተቀደሰ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም፥ ለእህል ቁርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በመለክያ ሁሉ ያገልግሉ ነበር።
የእህልም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ይሁን፤ ለመጠጥም ቁርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የሆነ የወይን ጠጅ ይቅረብ።
“እርሱም ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኃጢአት እንደ ቁርባኑ አድርጎ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ ክፍል መልካም ዱቄት ለኃጢአት መሥዋዕት ያመጣል፤ የኃጢአት መሥዋዕት ነውና ዘይት አያፈስበትም፥ ዕጣንም አይጨምርበትም።
እንዲህም በላቸው፦ ‘ለጌታ በእሳት የምታቀርቡት ቁርባን ይህ ነው፤ ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ።
“የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት መዓዛውም በሚያምር ዕጣን ላይ፥ ሁልጊዜም በሚቀርበው በእህሉ ቁርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ይሾም፤ ማደሪያውን ሁሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ መቅደሱንና ዕቃውን ይቆጣጠር።”
እርሱ እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት፥ አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት፥ ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ይህን ራሱን ባቀረበ ጊዜ አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታል።