ዘሌዋውያን 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 “እርሱም ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኃጢአት እንደ ቁርባኑ አድርጎ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ ክፍል መልካም ዱቄት ለኃጢአት መሥዋዕት ያመጣል፤ የኃጢአት መሥዋዕት ነውና ዘይት አያፈስበትም፥ ዕጣንም አይጨምርበትም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 “ ‘ሰውየው ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ለማቅረብ ዐቅሙ ካልፈቀደ፣ ስለ ሠራው ኀጢአት የኢፍ መስፈሪያ አንድ ዐሥረኛ የላመ ዱቄት ለኀጢአት መሥዋዕት ያቅርብ፤ ነገር ግን የኀጢአት መሥዋዕት ስለ ሆነ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አይጨምርበት፤ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 “አንድ ሰው ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ማቅረብ ባይችል፥ አንድ ኪሎ የላመ ዱቄት ስለ ኃጢአቱ ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርጎ ያምጣ፤ እርሱም ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት እንጂ የእህል መባ ስላልሆነ የወይራ ዘይት ወይም ዕጣን አይጨምርበት። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ለማምጣት ገንዘብ በእጁ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኀጢአት የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ ክፍል መልካም የስንዴ ዱቄት ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርባል፤ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና ዘይት አያፈስስበትም፤ ዕጣንም አይጨምርበትም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ለማምጣት ገንዘቡ ያልበቃ እንደ ሆነ፥ ስለ ሠራው ኃጢአት የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ ክፍል መልካም ዱቄት ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል፤ የኃጢአት መሥዋዕት ነውና ዘይት አያፈስስበትም፥ ዕጣንም አይጨምርበትም። Ver Capítulo |