Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 5:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሊቀ ካህናት ሁሉ ስለ ኅጢአት መባንና መሥዋዕትን ሊያቀርብ ከሰው ተመርጦ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾማልና፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እያንዳንዱ ሊቀ ካህናት ከሰዎች መካከል ይመረጣል፤ የእግዚአብሔርም በሆነው ነገር ላይ ሰዎችን በመወከል ለኀጢአት የሚሆነውን መባንና መሥዋዕትን ለማቅረብ ይሾማል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እያንዳንዱ የካህናት አለቃ ከሰዎች መካከል ተመርጦ ከእግዚአብሔር ጋር በሚያገናኛቸው ጉዳይ በሰዎች ፋንታ ሆኖ መባንና መሥዋዕትን ለማቅረብ ይሾማል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሊቀ ካህ​ናት ሁሉ ስለ ኀጢ​አት መባ​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሊያ​ቀ​ርብ ከሰው ተመ​ርጦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾ​ማ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሊቀ ካህናት ሁሉ ስለ ኃጢአት መባንና መስዋዕትን ሊያቀርብ ከሰው ተመርጦ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾማልና፤

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 5:1
17 Referencias Cruzadas  

“አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅባቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሚቀርበውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ እርሾ ያልነካው ቂጣ የሚቀመጥበትንም መሶብ ውሰድ፤


ሙሴም አሮንን፦ “ወደ መሠዊያው ቅረብ፥ የኃጢአትህንም መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፥ ለራስህና ለሕዝቡም አስተስርይ፤ ጌታም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቁርባን አቅርብ አስተስርይላቸውም” አለው።


እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሆነ ነገር የምመካበት አለኝ።


እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ለኀጢአታችን ሞተ፤


ሊቀ ካህናትም ሁሉ በየዕለቱ እያገለገለ እነዚያን ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን መሥዋዕቶች ደጋግሞ ለማቅረብ ይቆማል፤


እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድ መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፤


አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፤ በዚህም እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል።


ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።


እርሱ እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት፥ አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት፥ ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ይህን ራሱን ባቀረበ ጊዜ አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታል።


ሊቀ ካህናት ሁሉ መባንና መሥዋዕትን ሊያቀርብ ይሾማልና፤ ስለዚህ ይህም ካህን የሚያቀርበው አንድ ነገር ሊኖረው ግድ ነው።


እንግዲህ በምድር ቢኖርስ፥ እንደ ሕግ መባን የሚያቀርቡት ስላሉ፥ ካህን እንኳ ባልሆነም፤


ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ሲሆን፥ የሚቀርቡት መባና መሥዋዕት የሚያመልከውን ሰው ኅሊና ፍጹም የማያደርጉ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos