በዚህ ዓይነት ከመምሬ በስተ ምሥራቅ ማክፌላ የተባለው የዔፍሮን ቦታ የአብርሃም ርስት ሆነ፤ ይህም ቦታ እርሻውን፥ በውስጡ ያለውን ዋሻና በእርሻው ክልል ውስጥ ያለውን ዛፍ ሁሉን፤
ዘሌዋውያን 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህንም የበኵራት ቁርባን አድርጋችሁ ለጌታ ታቀርባላችሁ፤ እንደ መዓዛው ያማረ ሽታ ግን በመሠዊያው ላይ አይቃጠሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህን የበኵራት ቍርባን አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን ሽታው ደስ የሚያሰኝ ቍርባን ሆነው በመሠዊያ ላይ ለመቃጠል አይቀርቡም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየዓመቱ የመከር መጀመሪያ ከእህላችሁ በኲራት አድርጋችሁ የምታቀርቡትንም መባ ለእግዚአብሔር ታመጣላችሁ፤ እርሱ ግን በመሠዊያው ላይ አይቃጠል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህንም ዐሥራት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለበጎ መዓዛ በመሠዊያው ላይ አይቀርቡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህንም የበኵራት ቍርባን አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ እንደ ጣፋጭ ሽታ ግን በመሠዊያው ላይ አይቃጠሉም። |
በዚህ ዓይነት ከመምሬ በስተ ምሥራቅ ማክፌላ የተባለው የዔፍሮን ቦታ የአብርሃም ርስት ሆነ፤ ይህም ቦታ እርሻውን፥ በውስጡ ያለውን ዋሻና በእርሻው ክልል ውስጥ ያለውን ዛፍ ሁሉን፤
ይህንም ነገር እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች የእህሉንና የወይኑን ጠጅ የዘይቱንና የማሩንም፥ የእርሻውንም ፍሬ ሁሉ በብዛት ሰጡ፤ የሁሉንም አሥራት በብዛት አቀረቡ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከሩን ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤
ከየማደሪያችሁ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ከሆነ መልካም ዱቄት የተሠራ ሁለት የመወዝወዝ እንጀራ ታመጣላችሁ። ለጌታ ለበኵራት ቁርባን እንዲሆን በእርሾ ተቦክቶ ይጋገራል።
መጀመሪያ ከምታዘጋጁት ሊጥ አንድ እንጐቻ ልዩ ስጦታ የሆነ ቁርባን አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ከአውድማውም እንደ ልዩ ስጦታ አድርጋችሁ እንደምታቀርቡት ቁርባን እንዲሁ ታቀርቡታላችሁ።
እነሆም፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን ፍሬ በኵራት አቅርቤአለሁ።’ አንተም በአምላክህ በጌታ ፊት አኑረው፥ በአምላክህም በጌታ ፊት ስገድ።
እነዚህ ከሴቶች ጋር ያልረከሱ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበትም የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።