እነርሱም፦ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ትሩፋን በታላቅ መከራና በመሰደብ ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
ሰቈቃወ 5:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፥ ተመልከት ስድባችንንም እይ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኛ ላይ የደረሰውን ዐስብ፤ ውርደታችንን እይ፤ ተመልከትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! በእኛ ላይ የደረሰውን አስብ፤ ውርደታችንንም ተመልከት! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ የሆነብንን ዐስብ፤ ተመልከት ስድባችንንም እይ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፥ ተመልከት ስድባችንንም እይ። |
እነርሱም፦ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ትሩፋን በታላቅ መከራና በመሰደብ ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም። እናንት ወደ ጌታ አቤት፤ አቤት የምትሉ፤ ፈጽሞ አትረፉ፤
አቤቱ! አንተ ታውቃለህ፤ አስታውሰኝ ጐብኘኝም፥ የሚያሳድዱኝንም ተበቀልልኝ፤ ቁጣህንም ከማዘግየትህ የተነሣ እንዳታጠፋኝ፤ ስለ አንተ ስድብን እንደ ታገሥሁ እወቅ።
ካፍ። ሕዝብዋ ሁሉ እየጮኹ ያለቅሳሉ እንጀራም ይፈልጋሉ፥ ሰውነታቸውን ለማበርታት የከበረ ሀብታቸውን ስለ መብል ሰጥተዋል፥ አቤቱ፥ ተጐሳቁያለሁና እይ፥ ተመልከትም።
ሬስ። አቤቱ፥ ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፥ ዓመፃን ፈጽሞ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ፥ በሜዳ ሰይፍ ልጆቼን አጠፋ በቤትም ሞት አለ።
ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፥ ፍጻሜዋን አላሰበችም፥ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፥ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሏልና መከራዬን ተመልከት።
ሳምኬት። መንገድ አላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻልና፦ በውኑ የውበት ፍጻሜና የምድር ሁሉ ደስታ የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን? እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፥ ራሳቸውንም ያነቃንቃሉ።
ሬስ። አቤቱ፥ እይ፥ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት፥ ይበላሉን? በውኑ ካህኑና ነቢዩ በጌታ መቅደስ ውስጥ ይገደላሉን?
ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።