መሳፍንት 7:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሩበኣል የተባለው ጌዴዎን፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጠዋት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተ ሰሜን በኩል፥ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሩባኣል የተባለው ጌዴዎን፣ ከርሱም ጋራ የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጧት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተሰሜን በኩል፣ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱም ማለዳ ይሩባዓል የተባለው ጌዴዎንና ተከታዮቹ በጧት ማልደው ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያን ሰፈርም ከእነርሱ በስተሰሜን በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆ ውስጥ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌዴዎን የተባለውም ይሩበኣል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፤ በአሮኤድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ፤ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌዴዎን የተባለውም ይሩበኣል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፥ በሐሮድ ምንጭ አጠገብም ሰፈሩ፥ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ። |
በማግስቱም ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕት የሚሆን ዕንጨትን ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፥ ከእርሱም ጋር ሁለቱን አገልጋዮቹን እና ልጁን ይስሕቅን ይዞ፥ እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ተነሥቶ ጉዞ ጀመረ።
እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተ ምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊትለፊት፥ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን?
በዚህ ጊዜ ምድያማውያን ሁሉ፥ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች ያላቸውን አስተባብረው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር በኢይዝራኤል ሸለቆ ሰፈሩ።