Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 7:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጌታም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፥ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፤ “ምድያማውያንን በእጃቸው አሳልፌ እንዳልሰጥ ዐብረውህ ያሉት ሰዎች በጣም ብዙ ናቸው፤ እስራኤላውያን የገዛ ኀይላቸው እንዳዳናቸው በመቍጠር እንዳይታበዩብኝ፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፦ “በምድያማውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው ዘንድ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች ለእኔ እጅግ ብዙ ሆነዋል፤ በራሳቸው ኀይል የሚያሸንፉ ስለሚመስላቸው ለእኔ ክብር ከመስጠት ይቈጠባሉ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ከአ​ንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝ​ቶ​አል፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል፦ እጄ አዳ​ነኝ ብሎ እን​ዳ​ይ​ታ​በ​ይ​ብኝ እኔ ምድ​ያ​ምን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፥ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 7:2
25 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ለእስራኤል ጠራው። እርሱም፦ “እነሆኝ” አለ።


አሳም እንዲህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ ጌታ ጮኸ፦ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህምና፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ! በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና እርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ።”


የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፤ “‘ይህን ሁሉ ያደረግሁት በክንዴ ብርታት ነው፤ ደግሞም በጥበቤ አስተዋይ ነኝና። የመንግሥታትን ድንበር አፈረስሁ፤ ሀብታቸውን ዘረፍሁ፤ ነገሥታታቸውን እንደ አንድ ኀያል ሆኜ አዋረድሁ።


የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።


የሰው እብሪት ይዋረዳል፤ የሰውም ኩራት ይወድቃል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፤


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤


በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም እንዲህ ብለሃል፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር ልብ ተቀምጫለሁ፤ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።


ስለዚህ ለመረቡ ይሠዋል፥ ለአሽክላውም ያጥናል። በእነርሱ ድርሻው ሰብቷልና፥ መብሉም በዝቶአልና።


ጌታም፥ የዳዊትን ቤት ክብርና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር፥ በይሁዳ ክብር ላይ እንዳይታበይ የይሁዳን ድንኳኖች በቅድሚያ ያድናል።


እርሱም መልሶ፦ “ለዘሩባቤል የተባለው የጌታ ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ላኩ።”


በቅርንጫፎች ላይ አትመካ፤ ብትመካባቸው ግን ሥሩ አንተን ይሸከምሃል እንጂ ሥሩን አንተ አትሸከመውም።


ስለዚህ ትምክህት ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ? በሥራ ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በእምነት ሕግ ነው።


ነገር ግን ይህ ልዩ ኃይል የእግዚአብሄር መሆኑንና ከእኛ አለመመጣቱን ግልጽ ለማድረግ፥ ይህ ሀብት በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤


ማንም እንዳይመካ ከሥራ የመጣም አይደለም።


ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ ‘እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ ጌታ ይህን ሁሉ አላደረገም’ እንዳይሉ፥ ስለ ጠላት ትንኮሳ አሰብኩ።”


በልብህም፦ ‘ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን ሀብት አመጣልኝ’ እንዳትል፥ አስብ።


ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።


ስለዚህ፥ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” እንደሚል፥ የሚሰጠው ጸጋ ግን ከሁሉም ይበልጣል።


ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ ወደነዚያ ያልተገረዙ ሰዎች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም ጌታ ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን ጌታን የሚያግደው የለምና” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos