Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ጌዴ​ዎን የተ​ባ​ለ​ውም ይሩ​በ​ኣል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ማል​ደው ተነሡ፤ በአ​ሮ​ኤድ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ፤ የም​ድ​ያ​ምም ሰፈር ከእ​ነ​ርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረ​ብታ አጠ​ገብ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ይሩባኣል የተባለው ጌዴዎን፣ ከርሱም ጋራ የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጧት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተሰሜን በኩል፣ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ይሩበኣል የተባለው ጌዴዎን፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጠዋት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተ ሰሜን በኩል፥ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በማግስቱም ማለዳ ይሩባዓል የተባለው ጌዴዎንና ተከታዮቹ በጧት ማልደው ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያን ሰፈርም ከእነርሱ በስተሰሜን በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆ ውስጥ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ጌዴዎን የተባለውም ይሩበኣል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፥ በሐሮድ ምንጭ አጠገብም ሰፈሩ፥ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 7:1
14 Referencias Cruzadas  

አብ​ራ​ምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚ​ያች ምድር አለፈ፤ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በዚ​ያን ጊዜ በዚ​ያች ምድር ነበሩ።


አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ።


አሮ​ዳ​ዊው ሴሜይ፥ ሔሮ​ዳ​ዊው አል​ያቃ፥


አቤቱ፥ መታ​መ​ኔን እይ​ልኝ፥ ወደ ቀባ​ኸ​ውም ፊት ተመ​ል​ከት።


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


እነ​ር​ሱም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፥ ከፀ​ሐይ መግ​ቢያ ካለ​ችው መን​ገድ በኋላ በዓ​ረባ በተ​ቀ​መ​ጡት በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር፥ በጌ​ል​ጌላ ፊት ለፊት በረ​ዥሙ ዛፍ አጠ​ገብ ናቸው።


ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ እር​ሱና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከሰ​ጢም ተጕ​ዘው ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መጡ፤ ሳይ​ሻ​ገ​ሩም በዚያ አደሩ።


ኢያ​ሱም በማ​ግ​ሥቱ ማለዳ ተነሣ፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ጉን ታቦት ተሸ​ከሙ።


በዚ​ያች ቀንም መሠ​ዊ​ያ​ዉን አፍ​ር​ሶ​አ​ልና በዓል ከእ​ርሱ ጋር ይሟ​ገት ሲል ጌዴ​ዎ​ንን ይሩ​በ​ኣል ብሎ ጠራው።


ምድ​ያ​ምና አማ​ሌ​ቅም ሁሉ፥ የም​ሥ​ራ​ቅም ልጆች አንድ ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ፤ ተሻ​ግ​ረ​ውም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ሸለቆ ሰፈሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያች ሌሊት እን​ዲሁ አደ​ረገ፤ ጠጕሩ ብቻ ደረቅ ሆነ፥ በም​ድ​ሩም ሁሉ ላይ ጠል ወረደ።


የኢ​ዮ​አ​ስም ልጅ ይሩ​በ​ኣል ሄዶ በቤቱ ተቀ​መጠ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሩ​በ​ኣ​ልን፥ ባር​ቅ​ንም፥ ዮፍ​ታ​ሔ​ንም፥ ሳሙ​ኤ​ል​ንም ላከ፤ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም ካሉት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ እጅ አዳ​ኑ​አ​ችሁ፤ ተዘ​ል​ላ​ች​ሁም ተቀ​መ​ጣ​ችሁ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበ​ሰቡ፤ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos