ዮናስ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውኆች እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁ ባሕር ከበበኝ፥ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠመጠመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ፤ የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ ግን ሕይወቴን ከጕድጓድ አወጣህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ተራራዎች ሥር ወረድኩ፤ ከዚያ በታች ባለው ምድርም ውስጥ ለዘለዓለም ሊዘጋብኝ ነበር፤ አንተ ግን እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እኔን ከጥልቁ ውሃ አውጥተህ ሕይወቴን ታድናለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃ እስከ ነፍሴ ድረስ ፈሰሰ፤ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ከበበኝ፤ |
ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው?
የጥንት ሕዝብ ወዳሉበት ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር አወርድሻለሁ፥ የሚኖርብሽም እንዳይገኝ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ቀድሞ በፈረሰችው ስፍራ፥ በታችኛይቱ ምድር አኖርሻለሁ፤ ጌጥሽንም በሕያዋን ምድር አላኖርም።
ወደ ጉድጓድ በሚወርዱ በሰው ልጆች መካከል ሁላቸው ለታችኛው ምድር ለሞት አልፈው ተሰጥተዋልና በውኃ አጠገብ ያሉ ዛፎች ሁሉ በቁመታቸው እንዳይረዝሙ፥ ራሳቸውንም በደመናዎች መካከል እንዳያደርጉ፥ ውኃንም የሚጠጡ ኃያላኖቻቸው ሁሉ በቁመታቸው እንዳይቆሙ።
ቆመ፥ ምድርንም አንቀጠቀጣት፥ ተመለከተ፥ ሕዝቦችንም አስደነገጠ፥ የዘለዓለም ተራሮች ተናጉ፥ የጥንት ኮረብቶች አጎነበሱ፥ የጥንት መንገዶች የእርሱ ናቸው።