La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 7:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሥጋዬ ትልና ጓል ለብሶአል፥ ቆዳዬ ያፈከፍካል እንደገናም ይመግላል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አካሌ ቈስሎ ትልና ቅርፊት ለብሷል፤ ቈዳዬ አፈክፍኳል፤ ቍስሌም አመርቅዟል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መላ ሰውነቴ በትል ተሞልቶአል፤ ሥጋዬም በቅርፊት ተሸፍኖአል፤ ፈንድቶም ይመግላል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሥጋዬ በት​ልና በመ​ግል በስ​ብ​ሶ​አል፥ ቍስ​ሌን በገል እያ​ከ​ክሁ አለ​ቅሁ። ዐመ​ድም ሆንሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሥጋዬ ትልና ጓል ለብሶአል፥ ቁርበቴ ያፈከፍካል እንደ ገናም ይመግላል።

Ver Capítulo



ኢዮብ 7:5
15 Referencias Cruzadas  

እኔ እንደሚበሰብስ የተበላሸ ነገር፥ ብልም እንደሚበላው ልብስ ነኝ።”


መበስበስን፦ አንተ አባቴ ነህ፥ ትልንም፦ አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ ብያለሁ።


ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥ መላ ሰውነቴ እንደ ጥላ ሆነ።


አጥንቴ ከቁርበቴና ከሥጋዬ ጋር ተጣበቀ፥ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።


ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንደማይ አውቃለሁ።


ማኅፀን ትረሳዋለች፥ ትልም በደስታ ይጠባዋል፥ ዳግመኛም የሚያስታውሰው የለም፥ ክፋትም እንደ ዛፍ ይሰበራል።”


በአዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ፥ ልብሴም ይጸየፈኛል።


ከእግር ጥፍራችሁ እስከ ራስ ጠጉራችሁ ጤና የላችሁም፤ ቁስልና ዕባጭ እንዲሁም እዥ ብቻ ነው፤ አልታጠበም፤ አልታሰረም፤ በዘይትም አልለዘበም።


ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፤ በበታችህም ብል ተነጥፎአል፥ ትልም መደረቢያህ ሆኖአል ብለው ይመልሱልሃል።


ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።


በዚያም የረክሳችሁባትን መንገዳችሁንና ሥራችሁን ሁሉ ታስባላችሁ፤ ስለ ሠራችሁትም ክፋታችሁ ሁሉ ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።


ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያንጊዜ የጌታ መልአክ መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።