አስተምሩኝ፥ እኔም ዝም እላለሁ፥ የተሳሳትሁትንም ንገሩኝ።
“አስተምሩኝ፤ እኔም ዝም እላለሁ፤ ምኑ ላይ እንደ ተሳሳትሁ ጠቍሙኝ።
“አስተምሩኝ፤ እኔም ዝም እላለሁ፤ ስሕተቴንም አስረዱኝ።
“አስተምሩኝ፥ እኔም አዳምጣችኋለሁ፤ የተሳሳትሁትም ካለ አስረዱኝ።
እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ አትፍረድብኝ፥ የምትከራከረኝ ለምን እንደሆነ ንገረኝ።
ያለብኝስ በደልና ኃጢአት ምን ያህል ነው? መተላለፌንና ኃጢአቴን አስታውቀኝ።
“እነሆ፥ ቃላችሁን በትዕግሥት ጠበቅሁ፥ የምትናገሩትን ነገር እስክትመረምሩ ድረስ ሙግታችሁን አዳመጥሁ።
“እንግዲህ፥ ኢዮብ ሆይ፥ ንግግሬን እንድትሰማ፥ ቃሌንም ሁሉ እንድታደምጥ እለምንሃለሁ።
የማላየውን ነገር አንተ አስተምረኝ፥ ኃጢአትንም ሠርቼ እንደሆነ፥ ደግሜ አልሠራም የሚለው ማን ነው?
እነሆ፥ ይህችን መረመርን፥ የሰማነውም ይህ ነው፥ አንተም ለራስህ እወቀው።”
ወይስ፦ ከጠላቴ እጅ አስጥሉኝ፥ ወይስ፦ ከአስጨናቂው እጅ አድኑኝ አልኋችሁን?
የቅንነት ቃል እንዴት ኃይለኛ ነው! የእናንተ ሙግት ግን ምን ይገሥጻል?
አገልጋይህ ደግሞ ይጠብቀዋል፥ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።
አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፥ ዐይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።
የሚሰማን ጆሮ የሚገሥጽ ጠቢባዊ ምክር፥ እንደ ወርቅ ጉትቻ እንደሚያንጸባርቅም ዕንቁ ነው።
ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ይበልጡን ጠቢብ ይሆናል፥ ጻድቅንም አስተምረው፥ ይበልጡን አዋቂ ይሆናል።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ይህን አትርሱ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፥ ለመናገርም የዘገየ፥ ለቁጣም የዘገየ ይሁን፤
ሁላችንም በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በንግግሩ የማይሰናከል ማንም ሰው ቢኖር እርሱ ሰውነቱን ሁሉ መቈጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው።