ኢዮብ 5:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 እነሆ፥ ይህችን መረመርን፥ የሰማነውም ይህ ነው፥ አንተም ለራስህ እወቀው።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 “እነሆ፤ ይህን ሁሉ መርምረናል፤ እውነት ሆኖ አግኝተነዋል፤ ስለዚህ ልብ በል፤ ተቀበለውም።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 እኛ ይህን ሁሉ መርምረን እውነት መሆኑን ዐውቀናል አንተም አስተውለህ ተግባራዊ አድርገው።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 እነሆ፥ ይህን ዐውቀን መረመርን፥ የሰማነውም ይህ ነው፤ አንተ ግን አንዳች ሠርተህ እንደ ሆነ ለራስህ ዕወቅ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 እነሆ፥ ይህችን መረመርን፥ የሰማነውም ይህ ነው፥ አንተ ግን አንዳች ሠርተህ እንደ ሆነ ለራስህ እወቀው። Ver Capítulo |
ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥ የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።