ከአፉ ፋናዎች ይወጣሉ፥ የእሳትም ፍንጣሪ ይረጫል።
ነክቶት በሰላም የሚሄድ ማን ነው? ከሰማይ በታች ማንም የለም።
ከሰማይ በታች ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ ታዲያ፥ እንድመልስለት ለእኔ ያበደረ ማነው?
የከሰል እሳት እንደሚቃጠልበት ምድጃ ከአፍንጫው ጢስ ይወጣል።
ሲኦል በፊቱ ራቁትዋን ናት፥ ለጥፋትም መጋረጃ የለውም።
እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።
በውኑ አንተ ተቃውመኸዋልና ሽልማቱ አንተ እንደምትወድደው ይሆናልን? እኔ ሳልሆን አንተ ነህ የምትመርጠው፥ ስለዚህ የምታውቀውን ተናገር።
ጻድቅስ ብትሆን ምን ትሰጠዋለህ? ወይስ ከእጅህ ምንን ይቀበላል?
እንደ ፈላ ድስትና እንደሚቃጠል ሸምበቆ ከአንፍንጫው ጢስ ይወጣል።
ተራሮችን ይነቅላል፥ ነገር ግን አያውቁትም፥ በቁጣውም ይገለብጣቸዋል።
ሰማያት የጌታ ሰማያት ናቸው፥ ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።
የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥ የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም።
የዳዊት መዝሙር። ምድርና ሞላዋ የጌታ ናቸው፥ ዓለምና በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ።
ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና።
አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤
ወይስ ብድሩን እንዲመልስ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው?”
ምድር የጌታ ነውና፥ በእርሷ የሞላባት ሁሉ።
ማንም ግን “ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው፤” ቢላችሁ ይህን በነገራችሁ ሰው ምክንያትና በኅሊናም ምክንያት ሥጋውን አትብሉ፤
እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርሷም ያለው ሁሉ የጌታ የአምላክህ ነው።
እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ ቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ወደ ዮርዳኖስ ያልፋል።