በሰንሰለት ቢታሰሩ፥ ወይም በችግር ገመድ ቢጠመዱ፥
ነገር ግን ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣ በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣
ነገር ግን ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፥ ወይም በችግር ወጥመድ ቢያዙ፥
በሰንሰለት እጃቸውን የታሠሩ በችግር ገመድ ይያዛሉ።
እግሬንም በእግር ግንድ አግብተሃል፥ መንገዴንም ሁሉ ተቆጣጥረሃል፥ የእግሬንም ዱካ ወስነሃል።
እንግዲህ እግዚአብሔር ጥፋተኛ እንዳደረገኝ፥ በመረቡም እንደ ከበበኝ እወቁ።
የተቸገረውን በችግሩ ያድነዋል፥ በመከራም እንዲሱሙ ያደርጋቸዋል።
አሁን ከመከራ የምትፈተነው ለዚሁ ነውና፥ ወደ በደል እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
በጨለማ በሞትም ጥላ የተቀመጡ፥ በችግር በብረትም የታሰሩ፥
የሞት ገመዶች ወጠሩኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፥ ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ።
የኀጥኣን ገመዶች ተተበተቡብኝ፥ ሕግህን ግን አልረሳሁም።
ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት፥ አለቆቻቸውንም በእግር ብረት ያስሩ ዘንድ፥
የሞት ገመዶች ጠፍረው ያዙኝ፥ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፥
ክፉ በክፋቱ ይጠመዳል፥ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።
መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፥ ጐዳናዬንም አጣመመ።