ኢዮብ 36:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀብት ወደ ስድብ አስቶ እንዳይወስድህ፥ ትልቅ ጉቦም ከመስመር እንዳያስወጣህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለጠግነት እንዳያታልልህ፣ የእጅ መንሻ ብዛትም እንዳያስትህ ተጠንቀቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው በሀብት ብዛት እንዳያስትህ፥ በጉቦም እንዳይደልልህ ተጠንቀቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይበድሉ ዘንድ በተቀበሉት መማለጃ ኀጢአት ምክንያት ቍጣ በኃጥኣን ላይ ትመጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጣ ለስድብ አያታልልህ፥ የማማለጃም ብዛት ፈቀቅ አያድርግህ። |
ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ጥምቀት ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቁጣ እንድታመልጡ ማን አመለከታችሁ?
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።