ኢዮብ 34:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ በእኩለ ሌሊት በድንገት ይሞታሉ፥ ሕዝቡ ተንቀጥቅጦ ያልፋል፥ ኃያላንም ያለ ምንም ድካም ይወገዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እኩለ ሌሊት ላይ በድንገት ይሞታሉ፤ ሕዝብ ተንቀጥቅጦ ሕይወቱ ያልፋል፤ ኀያላኑም የሰው እጅ ሳይነካቸው ይወገዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች በእኩለ ሌሊት በቅጽበት ሊሞቱ ይችላሉ። ተንቀጥቅጠውም ያልፋሉ። ኀያላንም የማንም ሰው እጅ ሳይነካቸው ይወገዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚጮኸውንና ሰውን የማይሰማውን ከንቱ ነገር ያገኘዋል፥ በድሆች ላይ ክፉ አድርጎአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ በመንፈቀ ሌሊት በድንገት ይሞታሉ፥ ሕዝቡ ተንቀጥቅጦ ያልፋል፥ ኃያላንም ያለ እጅ ይነጠቃሉ። |
በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፤ ወደ አራራትም አገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፈንታ ነገሠ።
ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ፍርዳቸውም ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!