ኢዮብ 30:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፥ በጠንካራ እጅህም አሰቃየኸኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፤ በክንድህም ብርታት አስጨነቅኸኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅግ ጨከንክብኝ፤ በታላቅ ኀይልህም አሳደድከኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሕረት የሌላቸው ሰዎች ደበደቡኝ፥ የገረፈችኝ እጅም በረታች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፥ በእጅህም ብረታት አስጨነቅኸኝ። |
ውሽሞችህ ሁሉ ረስተውሃል አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ ጨካኝ ሰው እንደሚቀጣው ጠላትም እንደሚያቆስለው አቁስዬሃለሁና።