ኢዮብ 22:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጉዳዮችም ላይ ትመክራለህ፥ እርሱም ይሳካልሃል፥ ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያሰብኸው ይከናወንልሃል፤ በመንገድህም ላይ ብርሃን ይበራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕቅድህ ሁሉ ይሳካልሃል፤ መንገድህ ሁሉ ብርሃን ይሆንልሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጽድቅህንም ብድራት ይሰጥሃል። ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገርንም ትመክራለህ፥ እርሱም ይሳካልሃል፥ ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል። |
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥ ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ ከጋጣ እንደ ወጡ ጥጃዎች ትቦርቃላችሁ።