Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 90:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የጌታ አምላካችን ቸርነት በላያችን ይሁን። የእጆቻችንንም ሥራ በላያችን አቅና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የጌታ የአምላካችን ሞገስ በላያችን ይሁን፤ የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን፤ አዎን፣ ፍሬያማ አድርግልን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! በረከትህ ከእኛ ጋር ይሁን፤ የምናደርገውንም ሁሉ አሳካልን።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 90:17
15 Referencias Cruzadas  

በጉዳዮችም ላይ ትመክራለህ፥ እርሱም ይሳካልሃል፥ ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።


ግርማዊ ክብር ከልደትህ ጊዜ አንሥቶ፥ የተቀደሰ ሞገስም ከማኅጸን፥ የወጣትነትም ጠል የአንተ ነው።


አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፥ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና።


ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥ ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።


ከጽዮን፥ ከውበት ሙላቱ እግዚአብሔር ያበራል።


ወጣቱ ብንያም በጉልበቱ በዚያ አለ፥ ገዦቻቸው የይሁዳ አለቆች፥ የዛብሎን አለቆችና የንፍታሌምም አለቆች።


በኤፍሬምና በብንያም በምናሴም ኃይልህን አንሣ እኛንም ለማዳን ና።


ለጎረቤቶቻችን መከራከርያ አደረግኸን፥ ጠላቶቻችንም ይሣለቁብናል።


ሥራህን ለጌታ አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች።


አቤቱ ጌታ፥ ሥራችንን ሁሉ ሠርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ።


እንግዲህ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ሆነ ወይም የሚያጠጣ ቢሆን ምንም አይደለም።


እኛም ሁላችን፥ በመጋረጃ በማይሸፈን ፊት፥ የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን፥ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፥ ይህም መንፈስ ከሚሆን ጌታ የመጣ ነው።


ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና፥ የወደደን በጸጋም የዘለዓለምን መጽናናትና መልካሙን ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos