እንደ ጨለማም ወደ ጨለመች፥ ሥርዓትም ወደሌለባት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ፥ ልቀቀኝም።”
ኢዮብ 18:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብርሃን ወደ ጨለማ ያፈልሱታል፥ ከዓለምም ያሳድዱታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብርሃን ወደ ጨለማ ይጣላል፤ ከዓለምም ይወገዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብርሃን ወደ ጨለማ ይባረራል፤ ከሕያዋን ምድርም ይወገዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብርሃን ወደ ጨለማ አርቀው ያፈልሱታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብርሃን ወደ ጨለማ ያፈልሱታል፥ ከዓለምም ያሳድዱታል። |
እንደ ጨለማም ወደ ጨለመች፥ ሥርዓትም ወደሌለባት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ፥ ልቀቀኝም።”
ጠቅልሎም ያንከባልልሃል፥ ወደ ሰፊይቱም ምድር እንደ ኳስ ይወረውርሃል፤ አቤት፥ አንተ የጌታህ ቤት እፍረት! በዚያም ትሞታለህ፥ በዚያም የክብርህ ሠረገላዎች ይቀራሉ።
የገዛ ነውራቸውን አረፋ የሚደፍቁ እየባሰ የሚሄድ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም የተዘጋጀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።